'ከፍተኛ ስጋት' አውስትራሊያ እሥራኤልና ኢራን የሚገኙ ዜጎቿ እንደ አመቺነቱ አገራቱን ለቅቀው እንዲወጡ አሳሰስበች

የዩናይትድ ስቴትስ ባለስልጣናት እሥራኤል ኢራን ላይ ጥቃት መሰንዘሯን አስመልክተው ማረጋገጫ ሰጡ፤ ኢራን ግዛቷ ውስጥ ፍንዳታዎች መሰማታቸውንና በርካታ ድሮኖች መምከናቸውን አስታወቀች።

Planes.jpg

Smartraveller has warned Israel's Ben Gurion International Airport that operations could be paused on short notice. Credit: AAP, EPA / Abir Sultan

የዩናይትድ ስቴትስ ባለስልጣናት እሥራኤል የኢራን ከተማ በሆነችው ኢስፋሃን ወታደራዊ ጥቃት መፈፀሟን ገለጡ።

ባለስልጣናቱ እሥራኤል የባይደን አስተዳደርን ወታደራዊ ጥቃቷን ከመፈፀሟ ቀደም ብላ ትናንት ኤፕሪል 18 / ሚያዝያ 10 በመጪዎቹ 24 ወይም 48 ሰዓታት ውስጥ ጥቃት ልትፈፅም ማሰቧን እንዳስታወቀች ጠቁመዋል።

ወታደራዊ ጥቃቱን ተከትሎም አውስትራሊያውያን አመቺና ደህንነታቸውን ለአደጋ የማያጋልጥ ሁኔታ ካለ ኢራንና እሥራኤልን ለቅቀው እንዲወጡ የአውስትራሊያ ፌዴራል መንግሥት የጉዞ ማሳሰቢያ ሰጥቷል።

አውስትራሊያ ሁለቱም አገራት ከቀጣይ ወታደራዊ እርምጃዎች እንዲቆጠቡም አሳስባለች።

ጥቃቱን አስመልክቶ ከእሥራኤል በኩል የማረጋገጫም ሆነ ማስተባባያ መግለጫ አልተሰጠም።

ይህ በእንዲህ እንዳለም፤ የኢራን ፋርስ የዜና ኤጄንሲ "ሶስት ፍንዳታዎች" መሰማታቸውን ሲያመለክት፤ የአገሪቱ የሕዋ ኤጄንሲ ቃል አቀባይ ሁሴን ዳሊሬይን በበኩላቸው "በርካታ" ድሮኖች "ስኬታማ በሆነ ሁኔታ መክነዋል" ሲሉ ተናግረዋል።
Tehran.jpg
Credit: SBS News
ኢራን ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ከ300 በላይ ድሮኖች ወደ እሥራኤል ግዛት ወንጭፋለች።

ኢራን የድሮንና ሚሳይሎች ጥቃትን እሥራኤል ላይ ያደረሰችው፤ እሥራኤል ኤፕሪል 1 / መጋቢት 23 በሶሪያ የቆንስላ ጽሕፈት ቤቷ ላይ የአየር ጥቃት ሰንዝራ ሁለት ጄኔራሎቿን አክሎ የ12 ሰዎች ሕይወት መጥፋትን አስባብ በማድረግ እንደሁ ተዘገቧል።




Share
Published 19 April 2024 5:24pm
By Kassahun Seboqa Negewo, NACA
Source: SBS

Share this with family and friends