ለከፍተኛ ትምህርት ብድር ፕሮግራም ብቁ ነዎት?

Are you eligible for the Higher Education Loan Program?

Are you eligible for the Higher Education Loan Program? Credit: E+

ሶስት ሚሊየን ያህል አውስትራሊያውያን በከፍተኛ ትምህርት ብድር ፕሮግራም በኩል ከመንግሥት ተበድረዋል። ምናልባትም እርስዎም ሥራ እስከሚያገኙ ድረስ የዩኒቨርሲቲ ትምህርት ክፍያዎን ለማሸጋገር ብቁ ይሆኑ ይሆናል።


አንኳሮች
  • የከፍተኛ ትምህርት ብድር ፕሮግራም ሥራ እስከሚያገኙ ድረስ የዩኒቨርሲቲ ኮርስ ክፍያዎን ያዘገይልዎታል
  • የዓመት ገቢዎ $51,550 እስኪደርስ ድረስ ብድርዎን መክፈል አይጀምሩም
  • መመዘኛውን ለማሟላት የአውስትራሊያ ዜኘት ያለዎት ወይም የተለየ ቪዛ ወይም የመኖሪያ ፈቃድ ያለዎት መሆንን ግድ ይላል
  • ክፍያቸው ያልተፈፀመ የከፍተኛ ትምህርት ብድር ፕሮግራም ዕዳዎች ከሸማች ዋጋ ሠንጠረዥ ጋር አቻነት አድገዋል
በከፍተኛ ትምህርት ተቋም ውስጥ ሲመዘገቡ፤ ለኮርስዎችዎ የክፍያ ስምምነት ሊያበጁ ይገባል።

የተወሰኑ ተማሪዎች ዕዳን ለማስወገድ በቅድሚያ የኮርሶቻቸውን ክፍያዎች መፈፀም ሲችሉ፤ አብዛኛዎቹ ተማሪዎች ግና የትምህርት ክፍያዎቻቸው በመንግሥት እንዲሸፈንላቸው ያደርጋሉ። የመንግሥት የብድር ፕሮግራም፤ የከፍተኛ ትምህርት ብድር ፕሮግራም ተብሎ ይጠራል።

የከፍተኛ ትምህርት ብድር ፕሮግራም ዓይነቶች

አምስት ተለይተው ያሉ የከፍተኛ ትምህርት ብድር ፕሮግራም ዓይነቶች ዕቅዶች አሉ፤ የከፍተኛ ትምህርት አስተዋፅዖ-የከፍተኛ ትምህርት ብድር ፕሮግራም እና የከፊል-ሙሉ ክፍያ- የከፍተኛ ትምህርት ብድር ፕሮግራም በጣሙን ተዘውታሪ ናቸው።

እንደ የትምህርት መምሪያ ቃል አቀባይ ስቴፋኒ ስቶክዌል አባባል፤ ለከፍተኛ ትምህርት አስተዋፅዖ-የከፍተኛ ትምህርት ብድር ፕሮግራም ብቁ ለመሆን በጋራ ብልፅና የሚደገፍ ሥፍራ መመዝገብን ግድ ይላል።
በጋራ ብልፅና የሚደገፍ ሥፍራ አንድ ተማሪ ዩኒቨርሲቲ ሲመዘገብና መንግሥት ክፍያውን በቀጥታ ለዩኒቨርሲቲ ድጎማ በማድረግ የተማሪው ጠቅላላ የኮርስ ወጪ ሲቀንስ ነው።
ስቴፋኒ ስቶክዌል፤ የትምህርት መምሪያ ቃል አቀባይ
“ይሁንና ተማሪው የተወሰነ የኮርስ ክፍያን መክፈል ግድ ይለዋል፤ ያኔ ነው የከፍተኛ ትምህርት ብድር ፕሮግራም ጠቃሚ የሚሆነው” ይላሉ።
አያይዘውም “ምክንያቱም ብቁ ከሆኑ፤ የከፍተኛ ትምህርት ብድር ፕሮግራም በመውሰድ ቀሪውን ሂሳብ መክፈል ያስችላቸዋልና” ሲሉም ያስረዳሉ።

በሌላ በኩል፤ የከፊል-ሙሉ ክፍያ- የከፍተኛ ትምህርት ብድር ፕሮግራም የሙሉ ክፍያ ሥፍራ ምዝገባ ካደረጉ አውስትራሊያ ውስጥ ድጎማ ለማይደረግለት የዩኒቨርሲቲ ተቋም ሊውል ይችላል።

ለምን ዓይነት የከፍተኛ ትምህርት ብድር ፕሮግራም ብቁ እንደሚሆኑ አመዘጋገብዎ ይወስናል።

የከፍተኛ ትምህርት አስተዋፅዖ-የከፍተኛ ትምህርት ብድር ፕሮግራም እና የከፊል-ሙሉ ክፍያ- የከፍተኛ ትምህርት ብድር ፕሮግራም ብድሮች የሚሸፍኑት የሚወስዱትን ኮርስ ክፍያዎች ለመሸፈን ብቻ መሆኑን ልብ ማለት ጠቃሚ ነው።
How is your HELP debt calculated?
How is your HELP debt calculated? Source: Getty / Getty Images/Kanawa_Studio

ለከፍተኛ ትምህርት ብድር ፕሮግራም ብቁ ነዎት?

የግድ ሊያሟሉ የሚገባዎ፤
  • የአውስትራሊያ ዜግነት ቢያንስ የተወሰኑ ኮርሶችን አውስትራሊያ ውስጥ ከማጥናት ዕቅዶች ጋር  
  • ወቅታዊ ወይም የቀድሞ የኒውዚላንድ ልዩ ቪዛ መደብ ባለቤት ሆነው ለረጅም ጊዜ ነዋሪ መመዘኛዎች ብቁ የሆኑና ሙሉ ኮርሱን አውስትራሊያ ውስጥ ለማጥናት የወሰኑ መሆን  
  • ቋሚ ወይም የቀድሞ ሰብዓዊ ቪዛ ባለቤት ሆነው እስከ ኮርሱ ፍፃሜ ድረስ አውስትራሊያ ውስጥ የሚኖሩ ከሆነ  
  • የፓስፊክ ተሳትፎ ቪዛ ባለቤት ከሆኑ  
የባሕር ማዶ ባለሙያዎች የመሸጋገሪያ ኮርስ ለመውሰድ ተለይቶ የተመረጠ የከፊል-ሙሉ ክፍያ- የከፍተኛ ትምህርት ብድር ፕሮግራም ማግኘት ይችላሉ።

የከፍተኛ ትምህርት ብድር ፕሮግራም ብድርዎ የሚሰላው እንደምን ነው?

ክፍያዎች የሚከፈሉት በዓመት ሳይሆን በተወሰደው ኮርስ ልክ ነው። ተጨማሪ ኮርሶችን በወሰዱ ቁጥር ዕዳዎ በከፍተኛ ትምህርት ብድር ፕሮግራም ላይ ይታከላል።

ብሩስ ቻፕማን የአውስትራሊያ ብሔራዊ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ሃብት ጡረተኛ ፕሮፌሰርና የመጀመሪያው የከፍተኛ ትምህርት አስተዋፅዖ ሥርዓት ቀራጭ ናቸው።

“ለዲግሪ ከተመዘገቡ፤ በመጀመሪያው ሴሚስተር አራት ክፍሎችን ያጠናቅቃሉ እናም የሁሉንም ክፍሎች ዕዳ የሚጨምሩ ይሆናል”

“አንድ ዓመት ምናልባትም $3,000 ያስወጣዎት ይሆናል። ይሁንና በቀጣዩ ዓመት አንድ ኮርስ ብቻ የሚወስዱ ከሆነ ዕዳዎ የሚጨምረው በ $500 ያህል ብቻ ይሆናል” በማለት ያስረዳሉ።
Happy Australian students
Horizontal color image of a small group of Australian university students from different heritages and backgrounds. Credit: funky-data/Getty Images

ብድርዎን የሚከፍሉት እንደምን ነው?

ሥራ እስክሚያገኙ ድረስ ዕዳዎ አይነካም። አሠሪዎ ከእያንዳንዱ ደመወዝዎ የገቢ ግብር በሚቀንስበት ወቅት አነስተኛ ተጨማሪ ክፍያ ለከፍተኛ ትምህርት ብድር ፕሮግራም መክፈያ ይቀንሳል።

ይሁንና ይህ የሚሆነው ዓመታዊ ገቢዎ የተወሰነ መጠን ላይ ሲደርስ ነው።

በአሁኑ ወቅት፤ ያ ፤ ዕዳዎ ተከፍሎ እስከሚያልቅም ግብር በሚከፍሉበት ወቅት ከገቢ ግብርዎ ላይ ተጨማሪ አንድ ፐርሰንት ይታከላል።

ፕሮፌሰር ቻፕማን የከፍተኛ ትምህርት ብድር ፕሮግራምን ከዓለም አቀፍ ተማሪ ብድር ሥርዓት ስለሚለየው አንድ ጠቃሚ ፍረጃ ሲያስረዱ፤

“ሰዎች ችግር ውስጥ ገብተው ያሉ ከሆነ፤ ሥራቸውን ያጡ ወይም አረጋዊ ወላጅን ወይም አዲስ የተወለደ ልጅን የሚከባከቡ ከሆነ የፋይናንስ ሁኔታቸው ሲሻሻል መንግሥት ጠብቆ ስለሚቀበል መልሰው ስለ መክፈል ሊጨነቁ አይገባም" ይላሉ።

ስለምን፤ የእርስዎ የከፍተኛ ትምህርት ብድር ፕሮግራም ዕዳ ገቢዎን የሚጠባበቅ ነው፤ የሁሉም ሰው ገቢ ደግሞ ይለያያል። ማንኛውም የከፍተኛ ትምህርት ብድር ፕሮግራም ብድር ያለበት ሰው የተለየ የዕዳና ክፍያ አመዳደብ አለው።

በእዚህ መንገድ፤ የከፍተኛ ትምህርት ብድር ፕሮግራም ተበዳሪው በተወሰነ ጊዜ ውስጥ ከሚከፍለው ከባንክ ብድሮች እንደሚለይ ፕሮፌሰር ቻፕማን ያስረዳሉ።
ትምህርት አስተዋፅዖ ዕዳን ከፍተኛ ገቢ ያላችው የተወሰኑ ሰዎች በአምስት ዓመታት ጊዜያት ውስጥ መልሰው ሲከፍሉ፤ የተወሰኑቱ ከፍለው ሳይጨርሱ ከሥራ ዓለም ይሰናበታሉ።
ብሩስ ቻፕማን፤ በአውስትራሊያ ብሔራዊ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ሃብት ጡረተኛ ፕሮፌሰር
ምንም እንኳ የገቢ መጠን ደረጃ ላይ እስኪደርሱ ድረስ ዕዳዎን መልሰው ለመክፈል ግድ ባይሰኙም ዕዳዎ ግና ይንራል።

“ዕዳ ላይ የሚታከለው መጠን ማመላከቻ በሸማች ዋጋ ጠቋሚ ሠንጠረዥ መሠረት በየዓመቱ ይለያያል” ሲሉ ስቴፋኒ ቻፕማን ያስጠነቅቃሉ።

መንግሥት በበኩሉ ለተራዘመ ጊዜ ባሕር ማዶ የሚኖሩ ከሆነ ዕዳዎን ያስመልሳል። የውጭ አገር ገቢዎን የማስታወቅ ግዴታ ያለብዎት ሲሆን፤ የከፍተኛ ትምህርት ብድር ፕሮግራም በእዚያ መሠረት ግብር ላይ ይውላል።
The University of Sydney
The University of Sydney Source: AAP

"ማመልከት ቀላል ነው"

እንደ የአውስትራሊያ ዩኒቨርሲቲዎች ተጠባባቂ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሬኔ ሂንድማርሽ አባባል፤ ኮርስዎ ለሚፈጀው ጊዜ ማመልከት የሚያሻዎት አንድ ጊዜ ብቻ ነው።

“ለመመዘኛው ብቁ የሆኑ ተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት አስተዋፅዖ ከፍተኛ ትምህርት ብድር ፕሮግራም ጥያቄያቸውን ዩኒቨርሲቲው የሚያቀርብላቸው ቅፅ ላይ ሞልተው እንዲያቀርቡ ይጠየቃሉ። በቅፁ ላይም እንደ ታክስ ፋይል ቁጥር ወይም የታክስ ፋይል ቁጥር ማመልከቻ ማረጋገጫ፤ እንዲሁም የተማሪ ልዩ መለያቸውን ማስፈር ይጠበቅባቸዋል” ይላሉ።

የከፍተኛ ትምህርትዎን አስመልክቶ ስለ መንግሥት የፋይናንስ እገዛ ተጨማሪ መረጃ ካሹ ድረገጽን ይጎብኙ።


Share