ሐሰተኛ መረጃን መገደብ፤ ሐሰተኛ ዜናዎችን እንደምን መለየትና መፋለም እንደሚቻል

Hao blong faenem mo luk save kiaman nius o storian long Ostrelia

Hao blong faenem mo luk save kiaman nius o storian long Ostrelia Source: iStockphoto / nicoletaionescu/Getty Images

Get the SBS Audio app

Other ways to listen

መረጃ በብርሃን ፍጥነት በሚጓዝበት ዘመን፤ እውነትና ሐሰቱን ለመለየት አዋኪነቱ እየጨመረ መጥቷል። ሐሰተኛ ዜናዎች፣ ሐሰተኛ መረጃም ይሁን ወይም አሳሳች መረጃ ይባሉ መዘዞቻቸው ተመሳሳይ ነው፤ የሰዎችን አተያዮችና አመኔታዎች በማዛባት ሲልም ጠቃሚ ውሳኔዎች ላይ ተፅዕኖን ያሳድራሉ።


Key Points
  • ሐሰተኛ መጣጥፎችን በማጋራት አውስትራሊያውያን ከዓለም የከፉ ከሚባሉት አንዱ መሆናቸውን ጥናቶች ያሳያሉ
  • የቴክኖሎጂ ዕድገት በኦንላይን ተደራሽ የሆኑ ሐሰተኛ ዜናዎች ዕውነት መስለው እንዲታዩ አቅልሏል
  • ቀደምት አመኔታዎች ወይም ጥርጣሬዎች እርግጥ ሲሆኑ፤ ሐሰተኛ ዜናዎች ሰብዓዊ ባሕሪይ ላይ ብርቱ ተፅዕኖ ያሳድራል
በእኛ የዲጂታል ዘመን ሐሰተኛ መረጃ ብርቱ ጉዳይ ሆኗል።

በ RMIT ዩኒቨርሲቲ እውነታ ማረጋጋጫ ክፍል ተባባሪ ዳይሬክተር ሱሺ ዳስ አባባል፤ ሐሰተኛ መረጃ ሰዎች ባለማወቅ ለሌሎች የሚያጋሩት ትክክለኛ ያልሆነ መረጃ በሚል ይጠቀሳል።

በሌላ በኩል አሳሳች መረጃ፤ ሰዎች ሆን ብለው ሌሎችን ለማታለል የፈጠሩት ሐሰተኛ መረጃ ነው። ይህም ለተለያዩ ምክንያቶች ለቀልድ፣ የፖለቲካ አጀንዳን ለማራመድ ወይም በጠቆች አማካይነት ገንዘብ ለማግኘት ሲባል ይከወናል።

እንደ ሱሺ ዳስ እና ቡድናቸው ያሉ እውነታ አረጋጋጮች በእጅጉ በፍጥነትና በስፋት በማኅበራዊ ሚዲያ ስርጭት ላይ ያለ ጉዳይ ይዘት፤ ሐሰተኛ መረጃን ወይም አሳሳች መረጃን መያዝ አለመያዙን ለመለየት ክለሳ ያደርጋሉ።
የጉዳዩን ይዘት ትክክለኛነት ለማጣራት ምርምር ያካሂዳሉ። ይህም ትክክለኛ መረጃን ለሕዝብ መጋራቱን በማረጋገጡ ረገድ ያግዛል።

ወ/ሮ ዳስ አውስትራሊያ ውስጥ በርካታ የሐሰተኛ መረጃና አሳሳች መረጃ ቅይጦችን ለይተዋል። በአሁኑ ወቅት በአብዛኛው በማኅበራዊ ሚዲያ ሐሰተኛ የሆኑ ርዕሰ ዜናዎች እንደሚሰራጩም ሲናገሩ፤ 

"ለምሳሌ በአሁኑ ወቅት፤ በሩስያና ዩክሬይን መካከል ጦርነት አለ። እናም፤ በጦርነቱ ዙሪያ ሐሰተኛ መረጃና አሳሳች መረጃ አለ። መካከለኛው ምሥራቅ ውስጥም ሌላ ጦርነት አለ። እናም፤ የፍልስጤምና እሥራኤል ጉዳይ አለ፤ በእዚያም ዙሪያ በርካታ ሐሰተኛ መረጃዎችና አሳሳች መረጃዎች አሉ። እንዲሁም፤ የገንዘብ ማጭበርበሮችና ከጤና ጋር የተያያዙ ሐሰተኛ መረጃዎች አዘውትረን እያየን ነው" ብለዋል።
Left to right: Dr Timothy Graham, RMIT FactLab Sushi Das, Dr Darren Coppin.
Left to right: Dr Timothy Graham, RMIT FactLab Sushi Das, Dr Darren Coppin.

የማኅበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ 

የማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች ሁነኛ የማስታወቂያ መሳሪያ ሆነው ያገለግላሉ። መጠነ ሰፊ በሆነ መልኩም ለተግባቦት፣ ሃሳቦችንን ለመቀያየሪያና የተጠቃሚን የይዘት ፍላጎቶችና እንቅስቃሴዎች ልክን ተከትሎ በአልጎሪትም ትግበራ ተሳትፎና ፋይዳን ለማሳደግ ጥቅም ላይ ይውላል።  

ይሁንና፤ የዲጂታል ሚዲያ ተባባሪ ፕሮፌሰር የሆኑት ዶ/ር ቲሞቲ ግራሃም አልጎሪትሞች ባለማወቅ የሐሰት ዜናዎችንና የሐሰት መረጃን ማሰራጨት እንደሚችሉ ሲያስረዱ፤

"ሰዎች ወደ ጎን የማይሏቸው ይዘቶች ከየአቅጣጫው በግብአትነት ይደርሷቸዋል። ሰብዓዊ ፍጡራን በዘላቂነት የተያያዙ፣ እውነታ ባይኖራቸውም እንኳ በብዙኅን መገናኛ ለበለፀጉ ስሜት ቀስቃሽ ማኅበራዊና ስሜታዊ ይዘት የተቀረፁ ናቸው" ይላሉ።

አክለውም፤ የማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች ይዘቶችን ያጎላሉ፣ ያስተዋውቃሉ፣ ጠንካራ የተጠቃሚዎችን ግብረ ምላሾች ይፈጥራሉ፤ ሰዎች አሉታዊም ይሁኑ አዎንታዊ ብርቱ ስሜታዊ ምላሾችን የሚቀሰቅሱ ይዘቶችን ለማጋራት ይዳዳሉ።

ሐሰተኛ መረጃ እንደ ቀና ስህተቶች፣ ወገንተኛ ዘገባ፣ ስሜት ጫሪ፣ ሆን ተብሎ ከተነደፈ ፖለቲካ፣ ርዕዮተ ዓለም ወይም ምጣኔ ሃብታዊ አታላይነትን ከመሳሰሉ የተለያዩ ምንጮች ሊመጡ ይችላሉ።   

የሴራ ቃለ ነቢቦች በአብዛኛው ውስብስብ የሆኑ የምስጢር ሴራዎችን ያዘሉ ታሪኮችን ያካትታሉ። በአንፃሩ ሐሰተኛ መረጃ ሴረኛ ጉዳዮችን ያካተቱ ወይም ያላካተቱ መጠነ ሰፊ የሐሰት ወይም አሳሳች መረጃዎችን ያስፋፋሉ።

ለሴራ ቃለ ነቢብ አንድ ምሳሌ ሊሆን የሚችል በ RMIT የእውነታ ቤተ ሙከራ ቡድን አማካይነት አስመልክቶ ምርመራ ተካሂዷል።

ቃል ነቢቡ ይህ በ ተነሳሽነት የተጠነሰሰው የፋሽን ኢንዱስትሪው የበለጠ ዘለቄታ እንዲኖረው የተሴረና መንግሥት ሰዎችን በመከታተል እንዲቆጣጠር ነው ብሏል።

"ይህ የተሳሳተ ነው። ይህ ትክክል አይደለም። እኒህ ኮዶች ቁሶቹ የት እንደተሰሩ፣ ሥነ ምግባርን ተከተለው የተሠሩ ስለመሆንና አለመሆናቸው፣ የአስተጣጠብ መመሪያዎችና የጨርቅ ዝርዝሮችን የሚነግርዎት ናቸው። ይሁንና፤ እርግጥ ነው፤ ይህ ሁሉ እርስዎን ሊከታተልዎት ነው በሚል የሚከራከሩ ሰዎች አሉ" በማለት ዳስ ይናገራሉ።
Woman scanning a QR code from a label.
A woman is scanning a QR code from a label in a clothing store with her smartphone. Source: iStockphoto / javitrapero/Getty Images/iStockphoto

የሐሰተኛ መረጃ ተፅዕኖ

ሐሰተኛ መረጃ ቋንቋ መነገር ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ያለ ነው ሲሉ፤ ነዋሪነታቸው ሲድኒ የሆነው የባሕሪይ ሳይንቲስት ዶ/ር ዳረን ኮፒን ይገልጣሉ።   

ሆኖም፤ አሁን ጉዳዩ በሕብረተሰቡ ውስጥ በብርቱ በመስፋፋት ተፅዕኖ ያለው ሆኗል።  

ባለፉት ጊዜያት፣ ሰዎች የራሳቸውን ጭብጦች፣ እውነቶችና አመኔታዎች የሚያገኙት ከማኅበረሰባቸው፣ ከቤተሰብና ባሕል ነበር። አሁን ግና መረጃን የምናገኘው ከተለያዩ ምንጮችና ከመላው ዓለም ነው።  

ዶ/ር ኮፒን "እንደ አውስትራሊያውያን እውነታ አዘል ያልሆኑ መጣጥፎችን በማጋራት በዓለም ከከፉት ውስጥ አንደኛዎቹ ናቸው። 80 ፐርሰንቱ መጣጥፉ አጠራጣሪ ስለመሆኑ እንኳ ሳያስቡ ያጋራሉ። እናም ያ ተጋፍጠውን ያሉትን የቅጥፈት ዜናዎችና የሐሰት መረጃ ጉዳይን ማዛነቁ ግልፅ ነው" ይላሉ።

ሐሰተኛ መረጃ ወይም የሐሰት ዜናዎች ቀደም ሲል የነበሩ አመኔታዎችን ወይም ጥርጣሬዎችን እውነታን በማላበስ የሰብዓዊ ፍጡር ባሕሪይ ላይ ብርቱ ተፅዕኖ ስለማሳደሩ ይናገራሉ። ይህ ተፅዕኖም በቅጥፈት ዜናዎች ዘምሞ የሕዝባዊ ፖሊሲ ዕሳቤዎች ወደሚንፀባረቁበትና ፖለቲከኞች ለሕዝቡ ራሳቸውን ወደሚያቀርቡበት የምርጫ ድምፅ አሰጣጥ ይሻገራል።

ዶ/ር ኮፒን "በተለይም በኮቪድ ወቅት፤ በእያንዳንዱ የኮቪድ ገፅታዎች ሐሰተኛ መረጃን ተመልክተናል። ዋና ዳይሬክተርም 'የምንፋለመው ወረርሽኝን ብቻ አይደለም፤ የምንፋለመው የመረጃወረሽኝንም ጭምር ነው' ብለው ነበር" ሲሉ ተናግረዋል።

ዶ/ር ኮፒን አክለውም፤ ሰብዓዊ ፍጡራን በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ስለምን የሐሰት ዜናዎችን እንደሚያሰራጩ የሚቀጥሉትን ምክንያቶች ነቅሰው አንስተዋል።
የቅጥፈት ዜናዎች ሰብዓዊ ፍጡራን እርግጠኛ ያለመሆን ጥላቻን ተመርኩዞ ይተውናል። እኛ ፍፁም የሆነ ደህንነትና የተቆጣጣሪነት ስሜትን እንሻለን። እርግጠኛ አለመሆንን በመክላት ስሜት እንገፋፋለን። እናም፤ ምላሾችን ለማግኘት ፍለጋዎችን እናደርጋለን። ዝግጁ ሆነው ካለገኘናቸውም በክፍተት እንመላለን። ምንም በሌለበት ወቅት ለማናቸውም ዓይነት መረጃ እንነሆልላለን።
የባሕሪይ ሳይንቲስት፤ ዶ/ር ዳረን ኮፒን
እንደ አሳቸው አባባል፤ ሰብዓዊ ፍጡራን ባለፈው አዝጋሚ ለውጣችን ውስጥ አሉታዊ ምልከታ በጥልቀት ስር የሰደደ ነው። የእኛ በሕይወት የመቆየት ስሜት በተፈጥሮ ወደ ጨለምተኝነት እንድናጋድል ያደርገናል፤ እኒህ አደጋን የመጠንቀቅ ስሜት የከፋ ሁኔታ ሲገጥም ለትድግና ያበቃሉ።

"ከአንድ አውስትራሊያዊ ጋር አውግተው ከሆነና ቀደም ሲል ባሕር ማዶ ከነበሩ፤ በአብዛኛው ከውጭ አገር ሰው ጋር አብዝተው የሚያወጉት እዚህ ስላለው መልካም ዕድልና ውበት በመሆን ፈንታ፤ አውስትራሊያ ውስጥ ስላሉ ሸረሪቶች፣ እባቦችና ሻርኮች ነው" ነው ሲሉ ዶ/ር ኮፒን ይናገራሉ።

ሌላው የሐሰት ዜናን ወይም የሐሰት መረጃን ለማሳራጨት የምንከጅልበት ምክንያት ለራሳችን "ወገንተኛ ማረጋገጫ" ይሁንታን ለመቸር ስንል ነው።  

እንደ ዶ/ር ኮፒን አባባል፤ ክትባትን ከሚቃወም ቡድን ጋር የወገንን ከሆነ፤ ከእኛ አመኔታዎች ጋር ተስማሚ የሆነ መረጃን ወደ ማፈላለጉ እናመራለን፤ የሚታሰበን ያ ነው።  

ይበልጡን ልናስታውስ የምንችለው በብርቱ ወደሚነጣጥልና ፅንፈኛ ወደ ሆነ የእኛን ቀደም ብለው ያሉ አመኔታዎችን የሚያረጋግጥልንን መረጃ እንደሆነም ይናገራሉ።

ዶ/ር ኮፒን አክለውም፤ ለሐሰተኛ መረጃ በኦንላይን በቀላሉ መሠራጨትና እውነተኛ መስሎ ተደራሽ እንዲሆን ማስቻል የቴክኖሎጂ ዕድገት አንዱ ሌላ ለሐሰተኛ መረጃ መስፋፋት አስብባ መሆኑን ሲያመላክቱ፤

"ከሰዎችጋር ፊት ለፊት ተገናኝተው ሳለ፤ ቁጣቸው ወይም ያልተለመደ ባሕሪይ ወይም የሚያልብ መዳፎቻቸው፤ አመኔታ ቢስ ወይም የሚናገሩት ነገር ተአማኒነት የሌለው መሆኑን ይነግረናል" ይላሉ።
Puzzled Businesswoman reading a Text Message on her Smartphone
Misinformation can come from various sources, such as genuine mistakes, biased reporting, sensationalism, and intentional political, ideological, or economic manipulation. Source: iStockphoto / nicoletaionescu/Getty Images

የቅጥፈት ዜናዎችን መለየትና መፋለም

በዛሬው ዓለም የሐሰተኛ መረጃ መስፋፋትን ተከትሎ፤ እውነትንና ሐሰትን መለየት በጣሙን አስፈላጊ ሆኗል።  

ዜናዎችን የማጣራትና የመንቀስ ክህሎትን ማሳደግ ወሳኝ ነው።

ሱሺ ዳስ እውነተኛ ዜናዎችን ከሐሰተኛ ዜናዎች የመለየት ቀዳሚ ስትራቴጂያቸውን ሲያጋሩ፤  

"ጥቂት ቁልፍ ቃላቶችን ያግኙ፣ አዲስ የኦንላይን ገፅ ይክፈቱ፤ እኒያን ቃላቶች አዲሱ ገፅ ላይ በማስፈር እኒያን ቁልፍ ቃላት በመጠቀም ሌላ ምን ነገሮችን ሊያገኙ እንደሚችሉ ይመርምሩ። ተፅፎ ያለ መጣጥፍ ወይም እውነታ ማረጋገጫ መጣጥፍ ያለ እንደሁ ለመመልከት፤ እውነታ ማረጋገጫ የሚሉ ቃላቶችን በማከል የተወሰኑ ቁልፍ ቃላቶችን ያክሉ" በማለት ይመክራሉ።

ወ/ሮ ዳስ አያይዘውም፤ እየተመለከቱ ያሉት ምስል እውነተኛ ስለ መሆን አለመሆኑ እያስቡ ከሆነ፤ የጉግል ምስል መፈለጊያን ለማግኘት የኮምፒዩተሮን መጠቆሚያ ቀኝ አካል ጠቅ ያድርጉ ይላሉ።

እንዲሁም፤ የሐሰት መረጃ መስፋፋትን ለመፋለም ፍቱኑ መንገድ የሰለጠነ ውይይት ማካሄድ፣ ስድቦችን ከመጠቀም መቆጠብና ዘለግ ላለ ጊዜ ባለማቋረጥ እውነተኛ መረጃን ማቅረብ እንደሆነ ያስረዳሉ።

ለውጥ ትዕግስትን የሚጠይቅ አዝጋሚ ሂደት መሆኑን መገንዘብ አስፈላጊ ነው።

ዶ/ር ኮፒንም በበኩላቸው፤ ጥርጣሬ ፈጣሪ ዜናዎችን ወይም መረጃን በኦንላይን ከማጋራት በፊት በሙሉ አመኔታ አለመቀበል እንደሚያሻ ምክረ ሃሳባቸውን ሲለግሱ፤  

"ቆም ብለው ያስቡ፤ ይህን መድገም ይኖርብኛል ወይም ይህን በአደባባይ ሰዎች ፊት መናገር ይኖርብኛል? እናም እርግጠኛ ካልሆኑ ነገሮችን አይግፉ ወይም አያጋሩ። ስለምን የሐሰት መረጃን ተፅዕኖ የማባዛት አስተዋፅዖ እያደረጉ ነውና። በተጨማሪም፤ በሁለተኛ ደረጃ፤ የራስዎን ወገንተኝነት ከመፈለግ ይቆጠቡ" ብለዋል።  
Ol yangfala oli stap yusum phone blong olgeta long wan bikfala city
Experts believe the challenges of combating misinformation is set to grow with AI. Credit: We Are/Getty Images

የወደፊት አዝማሚያዎች

ቴክኖሎጂ እያደገ ሲሔድ፤ የሐሰት መረጃ መስፋፋትም ይዘምናል።

ፕሮፌሰር ቲሞቲ ግራሃም ያለማቋረጥ እየተለወጠ በሚሔደው የዲጂታል ዓለም የወደፊት ተግዳሮቶች ምን ሊሆኑ እንደሚችሉ ከወዲሁ ግምት ማሳደር እንዳለብን ያስረዳሉ።

ከተግዳሮቶቹ አንዱ የሆነው አርተፊሻል ኢንተለጀንስ የሚፈጥራቸው ይዘቶች በሰብዓዊ ፍጡር የተደረሱና በመጀመሪያ ዕይታም በእጅጉ አሳማኝ መስለው መታየት መቻል ነው።

ዶ/ር ግራሃም "ይህ ፅሁፍን ብቻ ሳይሆን፤ ግልፅ ነው ምስሎችንም ጭምር ነው። እውነተኛው ተግዳሮት በአርተፊሻል ኢንተለጀንስ የተፈጠሩ ይዘቶች መዛነቅና ከዕለት ወደ ዕለትም ምን ያህሉ እውነተኛ ምስሎች ወይም የተረጋገጡ ምስሎች ወይም የተረጋገጡ ፅሁፎች የሆኑና ያልሆኑ መሆኑን እግር ከእግር ተከታትሎ ለመለየት ውስብስብ መሆን ነው" ብለዋል። 

Share