ፊርማ አልባ ግና የትዳር ኑሮ? ይህ አውስትራሊያ ውስጥ ምን ማለት እንደሆነ እነሆ

Australia Explained - De Facto Relationships

rear view of a couple walking on the street Credit: franckreporter/Getty Images

Get the SBS Audio app

Other ways to listen

በአውስትራሊያ የቤተሰብ ሕግ መሠረት፤ ያለ ጋብቻ ፊርማ አብረው የሚኖሩ ጥንዶች ግንኙነት የሚታየው በጋብቻ ፊርማ የትዳር ኑሮ ጋር በተመሳሳይ መልኩ ነው። ይሁንና በመለያየት ወቅት ያሏቸው መብቶችና ግዴታዎች ምን ይሆናሉ? ከመነሻው ፊርማ አልባ የትዳር ኑሮን የመመሥረት መመዘኛዎችና ትሩፋቶች ምንድን ናቸው?


አንኳሮች
  • የፊርማ አልባ ግንኙነትን በተመለከተ፤ ያልተመዘገበ ከሆነ፤ የፍርድ ቤት ብይን ለሁሉም ተመሳሳይ አይደለም፤ በገለሰቡ ሁኔታ መሠረት የሚገመገም ይሆናል
  • የድኅረ-መለያየትን ጉዳዮችን ወይም የፍቅር ጓደኛ ሞትን ተከትለው የሚነሱ የይገባኛል ጥያቄዎችን አካትቶ፤ የፍርማ አልባ ተቋም ከለላ፣ ጋብቻ ያልፈፀሙ ጥንዶች መብቶች
  • ከፊርማ አልባ ግንኙነት መፍረስ በኋላ ሽምግልና ልዩነቶችን ለመፍታት የፍርድ ቤት አማራጭ ነው
አውስትራሊያ ውስጥ ሁለት ሰዎች ያለ ጋብቻ አንድ ላይ እንደ ጥንድ ሲኖሩ፤ ፍቅራዊ ግንኙነታቸው በሕግ ዕውቅና ይቸረዋል።

ፊርማ አልባ የትዳር ኑሮ በ ሁለት የተመሳሳይ ወይም ተቃራኒ ፆታ ያላቸው ሰዎች እንደ ጥንድ "እውነተኛ በሆነ የኑሮ መሠረት" ሲኖሩ የሚል ጥቅል ትርጓሜ ተሰጥቶታል።

የእርስዎን ፊርማ አልባ ግንኙነት ዕውቅና ለማስቸር ሂደቱና መስፈርቶቹ እንደሚኖሩበት ክፍለ አገር ወይም ግዛት ይወሰናል።

ለምሳሌ ያህል፤ ደቡብ አውስትራሊያ ውስጥ ፊርማ አልባ ግንኙነት በ ስር ምዝገባ አለው። አንዴ ለምዝገባ ከበቃ በኋላ በመላ አውስትራሊያ ወዲያውኑ ሕጋዊ ዕውቅና ይኖረዋል።
Australia Explained - De Facto Relationships
Lesbian couple looking at mobile phone and smiling in living room at home. Credit: eclipse_images/Getty Images
በሲድኒ የቤተሰብ ሕግ ተጠባቢ የሆኑት ኒኮል ኢቫንስ፤ ጥንዶች ስለምን ፊርማ አልባ የትዳር ኑሯቸውን ሕጋዊ ሰውነት ለማላበስ እንደሚመርጡ ሲያስረዱ፤

“ያ ምናልባትም ቪዛ ለማግኘት የሚሹ ሰዎችን ሊያግዝ ይችል ይሆናል፤ የፍቅር ወዳጃቸው በሞት በሚለይበት ወቅት ፊርማ አልባ ትዳር ላይ እንደነበሩ ለማረጋገጥ ከንብረት አኳያ ወይም ከሕክምና ረገድ በቅርብ ተጠሪ ከውሳኔ ላይ መድረስ ቢያሻ ለእክል ሊዳርጋቸው ይችላል።

“እንዲሁም፤ ከሕግ ወላጅ አኳያ፤ በተለይም በተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት ላሉ ሴቶች የቤተሰብ ሕግ በሚጠይቀው መሠረት ወላጅ ላልሆነች እናት የሕግ እናትነት ዕውቅንና ማግኘት ግድ ይላል። በፊርማ አልባ ግንኙነት መመዝገብ ወዲያውኑ ሕጋዊ ዕውቅናን ያላብሳል” ብለዋል።

በፊርማ አልባ ግንኙነት መመዝገብ እንደ ወጣት ግለሰብ ከወላጆች ተለይቶ በእራስ መኖርን በማመላከት የድጎማ መብቶችን ለመጠየቅ ያቀላል።

የፊርማ አልባ ግንኙነት ላይ የፍርድ ቤት ውሳኔ

ፍርድ ቤት ሁለት ሰዎች በፊርማ አልባ ግንኙነት ላይ ያሉ ጥንዶች ስለመሆናቸው እንዲያረጋግጡ ሲጠይቅ፤ የሚካተቱ ሁኔታዎች፤
  • የግንኙነታቸው የጊዜ ርዝመትና በሕዝብ ዘንድ ያላቸው ገፅታ
  • ወሲባዊ ግንኙነት ስለመኖሩ
  • ማናቸውም ዓይነት የፋይናንስ ድልድል ወይም የጋራ ንብረቶች
  • ለጋራ ሕይወት ያለ ቁርጠኝነት
ከውሳኔ ላይ ለመድረስ መመዘኛው እንደ ግለሰቡ ጉዳይ ይገመገማል፤ የፍርድ ቤት ሚዛን በቀረቡለት ሁኔታዎች ላይ ያመዝናል።

ወ/ሮ ኢቫንስ ፊርማ አልባ ግንኙነትን አስመልክቶ ሁለት የተሳሳቱ ዕሳቤዎች ከግንኙነቱ የጊዜ ርዝማኔ ጋር መያያዝ እንደሁ ሲገልጡ፤

“በርካታ ሰዎች ለፊርማ አልባ ባለ ትዳርነት ለሁለት ዓመታት አብሮ መኖር እንደሚገባዎ ይናገራሉ። ያ እውነት አይደለም። እንዲሁም አያሌ ሰዎች ከሁለት ዓመታት በኋላ ግንኙነታችሁ ፊርማ አልባ ትዳር እንደሆነ አድርገው ያስባሉ። በድንገት ከዚያ በኋላ ለ50% የንብረት ክፍያ ብቁ እንደሆኑ ያስባሉ፤ ያም፤ እንደገና እውነት አይደለም።”
Australia Explained - De Facto Relationships
A Young Man is Distraught and Ignoring her Muslim Girlfriend While Arguing. A Man and his Muslim Girlfriend are Having a Serious and Harsh Communication Due to the Problems They are Going Through. Credit: ProfessionalStudioImages/Getty Images
ከሁለቱ ግለሰቦች አንደኛው በሕጋዊ መንገድ ያገባ ቢሆን እንኳ በአቻ የሕግ ጉዳይ ፊርማ አልባ የትዳር ኑሮ ስለመኖሩ ዕውቅና ያደርጋል።

የቤተሰብ ሕግ ተጠባቢ የሕግ ባለሙያ የሆኑት ዳሚየን ግሪር ይህንን ሲያስረዱ፤

“በጣሙን አዘውትሮ አይሆንም። ይበልጡኑ ተጋብተው የነበሩ ሰዎች ጋብቻቸው ፈርሶ ለፍቺ ፍርድ ቤት ሳያመለክቱ ይቀሩና አንዳቸው ወደ ፊርማ አልባ የትዳር ኑሮ ያመራሉ።” ይላሉ።

የፊርማ አልባ የትዳር ኑሯቸው ፈርሶ ልጆችን አስመልክቶ የወላጅ ክርክሮችን አስመልክቶ ያላቸው ጉዳይ በፍርድ ቤት የሚታየው ልክ በጋብቻ ሥርዓት ተጋብተው እንዳሉ ጥንዶች ነው።

የፊርማ አልባ ጥንዶች በጋብቻ ሥርዓት እንዳሉቱ በግንኙነት ላይ ሳሉ በማናቸውም ወቅት አሳሪ የፋይናንስ ስምምነት ሊያደርጉ ይችላሉ።

ይህንን በተመለከተ ኒኮል ኢቫንስ ሲያስረዱ፤

“ሰነዶች ላይ የሰፈሩት ሁለታችሁም ወደ ግንኙነቱ ያመጣችኋቸው ንብረቶችና ዕዳዎች በመለያየት ወቅት እንደምን መካፈል እንዳለባችሁ ይወስናሉ።
 
አሳሪ የፋይናንስ ስምምነት ሊዘጋጅ የሚችለው በሕግ ባለሙያ ብቻ ነው።

“የሕግ ባለሙያው ወደ እንዲህ ዓይነቱ ስምምነት የገባችሁት ጉዳቶችና ጥቅሞችን በተመለከተ ገለልተኛ የሆነ የሕግ ምክር ተሰጥቷችሁ ነው የሚል ሰነድ ላይ መፈረም አለበት” ብለዋል።

በሽምግልና የክርክር አፈታት

በጋብቻ ሥርዓት እንዳሉ ጥንዶች ሁሉ ፊርማ አልባ ጥንዶችም ሲለያዩ በተመሳሳይ መልኩ ልጆችና ፋይናንስን አስመልክቶ ከስምምነት ላይ ለመድረስ የሽምግልና አገልግሎትች ማግኘት ይችላሉ።

በምዕራብ አውስትራሊያ የጋብቻ አውስትራሊያ አማካሪ ፊዮና ቤኔት አባባል ሽምግልና በስሜት ሳይገፉ ሁለቱንም ሰዎች ፍትሐዊና ገለልተኛ ከሆነ ስምምነት ላይ ያደርሳል።

ድህረ-መለያየት፤ የንብረት ክፍፍልንና የገንዘብ ድጎማን አስመልክቶ ፍርድ ቤት በፋይናንስ ጉዳዮች ላይ ትዕዛዞችን ያሳልፋል።
Australia Explained - De Facto Relationships
Family law concept. Family Paper and hammer on the table Source: Moment RF / Rapeepong Puttakumwong/Getty Images
እንዲህ ባሉ ጉዳዮች ላይ የፍርድ ቤት ትዕዛዞችን ለማስወጣት ከፊርማ አልባው ግንኙነት በተለያዩ ሁለት ዓመታት ጊዜያት ውስጥ ማመልከቻዎችን ማስገባት ግድ ይላል።

አቶ ግሪር “ከጊዜ ገደብ ውጭ ለመከወን ፍርድ ቤትን መጠየቅ ይችላሉ። ይሁንና ሌሎች ሊያነሷቸው የሚገቡና ይበልጡን ውስብስብ የሆኑ ጉዳዮች አሉ” ይላሉ።

በአማራጩ፤ የቀድሞ ፍቅረኞች ከጋራ ስምምነት ላይ የግድ መድረስ አለባቸው፤ ሆኖም ስምምነቱ ሕጋዊነት ያለውና ሰነድ ላይ የሠፈረ መሆን አለበት።

“እናም ሰነዶች ላይ የማስፈሪያ ሁለቱ መንገዶች አንድም የፋይናንስ ጉዳዮችን አስመልክቶ ፍርድ ቤቱ ይሁንታን የተላበሱ ትዕዛዞችን በመስጠት ሲሆን፤ ሌላኛው እራስዎ ከፋይናንስ ስምምነት ላይ መድረስ በመቻል ነው” ሲሉ አቶ ግሪር አክለው ያስረዳሉ።

የሽምግልና ሂደት ፈቃደኝነት ላይ የተመሠረተ ነው። አንደኛው ግለሰብ ተነስሽነትን ሲወስድ፤ አገልግሎቱ ሌላኛው ግለሰብ ለመሳተፍ ፈቃደኛ ይሆን እንደሁ ይጠይቃል።
Australia Explained - De Facto Relationships
A father is standing in the doorway of their home with his son as they say goodbye to the mother who is going to work. Credit: SolStock/Getty Images
ሁለቱም ግለሰቦች ለመቀጠል ከተስማሙ፤ የተጋላጭነት መንስኤዎችን አክሎ የግንኙነቱን ታሪክ ለመረዳት የማጣራት ሂደት ይከተላል።

ወ/ሮ ቤኔት ይህን ሲያስረዱ፤

“እኒህ ሁለት ሰዎች በአንድ ክፍል ውስጥ አብረው ቁጭ ማለት ይችሉ እንደሁ ለመረዳት እንሻለን ወይም አንድ ክፍል ውስጥ ቁጭ ማለት ካልቻሉ ቢያንስ በሸምጋይ አማካይነት መነጋገር ይችላሉን?

“እናም ሽምግልናው ከመጀመሩ በፊት የቤተሰብና የቤት ውስጥ አመፅ ወይም አስገዳጅ ቁጥጥር ቀደም ሲል መኖር አለመኖሩን እርግጠኞች ለመሆን በእዚያ ረገድ ተጋላጭነትን እናጣራለን” ይላሉ።

በመጨረሻም፤ ለተለያዩ ጥንዶች ሽምግልናን የመቀበሉ ትሩፋት ልዩነቶቻቸውን አቅም በተመላው መንገድ እንዲፈቱት ማስቻል ነው።

“ከፍርድ ቤት ከጀመሩ መከወኛ በመሆን በጣሙን ተቃውሞ የበዛበትና የጭቅጭቅ ሂደት ይሆናል።
Australia Explained - De Facto Relationships
An interracial married couple talks to therapist together about their life. The asian woman tried to explain how he won't listen to her. Her husband looks at the floor in embarrassment. Credit: FatCamera/Getty Images
“በሽምግልና የመጡ ከሆነ ግና ከሌላኛው ግለሰብ ዕይታ አኳያ ምን መመልከት እንደሚችሉ ማወቅ ይችላሉ። እግረ መንገዱን ሰዎች ምን ማድረግ እንዳለባቸው ከመነገር ይልቅ ጉዳዩን እራሳቸው መፍታት የሚችሉ መሆኑ እንዲሰማቸው ያደርጋል፤ ትምህርት ይበረከትበታል።” ሲሉ ያስረዳሉ።

በሚኖሩበት ክፍለ አገር ግንኙነቶችን አስመልክቶ ለጠቅላላ መረጃና መመሪያ የሕግ ባለሙያ ለመፈለግ የቪክቶሪያ የሕግ ሕብረተሰብና የኩዊንስላንድ ሕግ ሕብረተሰብን ጨምሮ በኔው ሳውዝ ዌልስ የሕግ ሕብረተሰብ ተነሳሽነትና በመላ አውስትራሊያ በሌሎች የሕግ ሕብረተሰባት የሚደገፈውን ድረ-ገፅን ይጎብኙ።

የቤተሰብ ግንኙነት ጉዳዮችንና አገልግሎቶችን በተመለከተ ድጋፍ ስለሚቸረው የአውስትራሊያ መንግሥት መረጃ ካሹ ድረ-ገፅን ይጎብኙ ወይም 1800 050 321ይደውሉ።

ቀውስ ውስጥ ነዎት?

ለድንገተኛ 000 ይደውሉ|ላይፍላይን 13 11 14|ብሔራዊ የፆታ ጥቃት፣ የቤት ውስጥ አመፅ የምክር አገልግሎት 1800 737 732.

Share