በነባር ዜጎች መካከል ያለ ባሕላዊ ዝንቅነትን የመረዳት ጠቀሜታ

Cultural Diversity.jpg

Portrait of three generation Aboriginal family. Credit: JohnnyGreig/Getty Images

Get the SBS Audio app

Other ways to listen

የአውስትራሊያ ነባር ዜጎች ከሆኑት የአቦሪጂናልና ቶረስ መሽመጥ ደሴት ሰዎች ጋር ተሳትፎ በማድረግ ትርጉም ያለው ግንኙነቶችን ለመገንባት ካሹ በመካከላቸው ያሉ ባሕላዊ ዝንቅነቶችን መረዳት ግድ ይላል።


አንኳሮች
  • የአውስትራሊያ ነባር ዜጎች አንድ ወጥ አገር በቀል ቡድን አይደሉም
  • 500 ያህል ብሔሮች አሏቸው፤ እያንዳንዳቸው የተለያዩ ባሕሎች፣ ቋንቋዎች፣ የአኗኗር ዘይቤዎችና የዝምድና መዋቅሮች ያላቸው ናቸው
  • ከነባር ዜጎች ጋር ትርጉም ያላቸው ግንኙነቶችን ለመገንባት ዝንቅነትን መረዳት ወሳኝ ነው
በአውስትራሊያ ነባር ዜጎች መካከል በልፅጎ ያለው ዝንቅነት ማራኪ ገፅታን የተላበሰ ሲሆን፤ ሁሉንም የአቦርጂናልና ቶረስ መሽመጥ ደሴተኛ ሰዎች አንድ ወጥ ቡድን አድርጎ የመመልከቱን የተሳሳተ ግንዛቤ አሌ የሚል ነው።

ነባር ዜጎች ባሕላዊ ጌጥነትን፣ ቋንቋዎችን፣ የአኗኗር ዜይቤዎችንና የዝምድና መዋቅሮችን ወካይ ናቸው።

ይህን ዝንቅነት ከሚያጠቃልሉ ማለፊያ መንገዶች አንዱ ን መመልከት ነው።

በምዕራብ አውስትራሊያ ኪምበርሊ ቀጠና የባራዲዋዋ አክስት ሙንያ አንድሩስ ሲያስረዱ፤

“ሰዎችን እንጋብዛለን፤ ስለምን 500 ያህል ብሔሮች በእዚያ ካርታ ላይ ሰፍረው አሉና። እያንዳንዱ ብሔር የራሱ የሆነ ወይም ከሌሎች ጋር የሚጋራቸው ቋንቋ አለው” ሲሉ።
Carla Rogers and Aunty Munya Andrews.jpg
Carla Rogers (left) and Aunty Munya Andrews (right), Evolve Communities. Credit: Evolve Communities
800 የአነጋገር ዘዬዎችን ከባሕሎቻቸው ጋር፣ የአኗኗር ዘይቤዎችን፣ የዝምድና መዋቅሮችን ያካተቱ ከ250 በላይ የነባር ዜጎች ቋንቋዎች አሉ። ሁሉም ብሔሮች በሥነ ጥበብ ሳይቀር ይለያይሉ" በማለትም አክስት ሙንያ አክለው ይስረዳሉ።

“የነባር ዜጎች ሥነ ስዕልን በመመልከት ብቻ ከየትኛው አካባቢ የመጣ እንደሁ ለይቼ አውቃለሁ። ያን ያህል የተለየ ስለሆነ። አያሌ ሰዎች የነጥብ ቅብን ከአቦርጂናል ባሕል ጋር ያያዩዝታል፤ ይሁንና ያ የአንድ ብሔር ብቻ ነው።

“የእኔን ሰዎች፤ የባርዲ ሰዎችን ስትመለከቱ፤ እኛ የጨው ውኃ ሰዎች ነን። ሥነ ስዕሎቻችን ከሌሎች በዓለም ዙሪያ ካሉ ደሴተኞች ጋር በጣሙን ተመሳሳይ ነው። ወጀቦችን በግልፅ የሚያሳዩት ጂኦሜትሪክ ቅቦቹ ከቶውንም የነጥብ ቅቦች አይደሉም" ብለዋል።

አክስት ሙንያ፤ ደራሲት፣ ጠበቃና የተዛማጅ ማኅበረሰባት ተባባሪ ዳይሬክተር ናቸው። ሰዎች ከነባር ዜጎች ጋር በሚወያዩበት ወቅት 'አንድ ወጥ መጠን ለሁሉም ልክ አይሆንም' የሚለውን ይትባሃል ልብ ሊሉ እንደሚገባ ይናገራሉ።

ይበልጥ ትርጉም ያላቸው ግንኙነቶችን ለመገንባት ለማኅበረሰብ ወጎችና ልማዶች ከበሬታን መቸር ወሳኝ የመጀመሪያ እርምጃ ነው።

ካርላ ሮጀርስ ከአክስት ሙንያ ጋር በአጋርነት የሚሠሩ ነባር ዜጋ ናቸው። የአውስትራሊያን የጋርዮሽ ታሪክና ነባር ዜጎች በሆኑና ባልሆኑቱ መካከል ያሉ ክፍተቶች እንደምን እስካሁን ዘልቀው እንዳሉ የመሰለ ዕውቀትን መረዳት ወሳኝ መሆኑን ያሳስባሉ።

“ለመጀመሪያ ጊዜ አውስትራሊያ በቅኝ ግዛት ስር በወደቀችበትና አሁንም ቀጥሎ [አለ]፣ ዋነኛው ችግራችን የዝንቅነት ግንዛቤ ማነስ ነው። አሁን ድረስ ተከስተው ያሉት አብዛኛዎቹ ችግሮቻችን የአቦርጂናልና ቶረስ መሽመጥ ደሴት ሰዎችን አንድ ወጥ ቡድን አንድ አድርጎ መመልከትና በለፅጎ ላለ ዝንቅነት ዕውቅናን አለመቸር ነው” ይላሉ።
Indigenous people.jpg
The Indigenous peoples of Australia are not one homogenous group. Credit: Belinda Howell/Getty Source: Moment RF / Belinda Howell/Getty Images

አውስትራሊያ ሁሌም መድብለባሕላዊት ናት

አክስት ሙንያ ነባር ዜጎች የመድብለባሕል "ተጠባቢዎች" እንደሆኑ ሲናገሩ፤

“የእኔ ሰዎች ከመድብለባሕላዊነት ጋር ለሺህ ዓመታት ቆይተዋል። ከሌሎች የአቦርጂናል ቡድናት ጋር መቀራርብን ተምረናል፤ የተወሰኑ የተለዩ ቋንቋዎችንም ለምደናል” ይላሉ።

እንደ ዶ/ር ማሪኮ ስሚዝ ላሉ የነባር ዜጋ ዝርያ ያላቸውና የአውስትራሊያ ነባር ዜጎችን ዝንቅነት ለሚያበለፅጉቱ ዕውቅናን መቸር ጠቃሚ ነው።

አባታቸው ከኒው ሳውዝ ዌይልስ ዩን ብሔር ሲሆኑ፤ እናታቸው ከጃፓን ከዩሹ ኮኩራ ናቸው።

“የተወሰኑ ሰዎች በጃፓናዊና አቦርጂናል ዝርያዬ ሳቢያ የጃፓናውያን የዕንቁ ኢንዱስትሪ ከነበረበት ከላይኛው ሰሜንና ሰሜን ምዕራብ አውስትራሊያ እመስላቸዋለሁ።

“ይሁንና ወላጆቼ የተገኛኙት አባቴ ጃፓን ውስጥ ሲዘዋወር ከአንዲት የከዩሹ ቡና መሸጫ ውስጥ ነው። ጃፓን ውስጥ ተጋቡ። አባቴ እናቴን ወደ አውስትራሊያ ይዟት መጣ” ሲሉ አውግተዋል።

ዶ/ር ስሚዝ ሲያድጉ የእስያዊት ገፅታ ስላላቸው አያሌ “የዘረኝነት ስድቦች” ተሰንዝረውባቸዋል፤ ከቶውንም ሰዎች አቦርጂናል መሆናቸውን ሲያውቁ አተያዮቻቸው "ከፍ ወዳለ ደረጃ" አሻቅቧል።
Dr Mariko Smith .jpg
Dr Mariko Smith. Credit: Anna Kucera/Anna Kucera
ዶ/ር ስሚዝ፤ ለእዚያም አስባቡ ሰዎች ነባር ዜጎችን አስመልከቶ እንደ ቆዳ ቀለም ወይም የስልጣኔ ደረጃን በተመለከተ ከተፃፈ ታሪክ የቀሰሟቸው የጅምላ ዕይታና ጠባብ ግምቶች ስላሏቸው ነው በማለት ሲያመላክቱ፤

“ሰዎች ምናልባትም ቀደም ሲል በሕይወት ዘመናቸው ከአንድም የአቦርጂናል ሰው ጋር ተገናኝተው እንደማያውቁ ያስቡ ይሆናል፤ ይሁንና ተገናኝተው የማወቃቸው አጋጣሚ ግና አለ። ከጅምላ ዕይታዎቻቸውና ግምቶቻቸውን ጋር አልገጥም ብሏቸው ይሆን እንጂ” ይላሉ።

ዶ/ር ስሚዝ ፤ የአሁኒቷ አውስትራሊያ መድብለባሕላዊት መሆንንና እውነተኛ አካታች የሆነውን የነባር ዜጎች ዝንቅነት አድናቆትን ልትቸር ይገባል በማለት ሲያክሉ፤

“ስለ ነባር ዜጎች በጣሙን እዚህ ግባ በማይባሉ መንገዶች የሚያስቡ ከሆነ፤ መፍትሔዎቹም እዚህ ግቡ የማይባሉ ይሆናሉ። ውስብስብ፣ ዝንቅ፣ ዕሳቤ ሁሉን አቀፍ፣ ዝንቅ መፍትሔዎችንና ዕሳቤዎችንም እንዲሁ ይሻል” ብለዋል።

ካርላ ሮጀርስ፤ ዝንቅነትን የማይረዱ ነባር ዜጋ ያልሆኑ ሰዎች ስሕተቶችን እንደሚሠሩ ሲያመላክቱ፤

“በጣሙን ጎጂ የሆኑ፣ ዘረኝነትን የተላበሱ ዓይነት አባባሎችን ልንናገር እንችላለን። የግንዛቤ ጋሬጣ ነው” ሲሉ።
Aboriginal and Torres Strait Islander people.jpg
Thirteen Aboriginal and Torres Strait Islanders from across Australia are participating in the inaugural Mob in Fashion initiative. Credit: Thirteen Aboriginal and Torres Strait Islanders from across Australia are participating in the inaugural Mob in Fashion initiative.

ስለ አገር በቀል ዝንቅነት የበለጠ መማር የምንችለው የት ነው?

ወደ አውሮፓ ሲጓዙ እንደሚያደርጉት ሁሉ ከካርታ ይጀምሩ፤ ያሉበትን ብሔር ይለዩ፤ እናም ባሕልና ቋንቋዎቻቸውን ይማሩ።

ሮጀርስ “ከሁለት ሰዓታት በላይ የሚጓዙ ከሆነ፤ እንበልና ከሲድኒ አንስተው ሲጓዙ የተለያዩ ብሔሮችን በማቋረጥ ነው” ይላሉ።

ልማዳዊ ባለቤቶችንና ታሪክን አካትተው፣ ስለ ብሔሩ ጥልቅ ዕይታ እንዲኖርዎት፤ የመሬት ምክር ቤትና የአካባቢ ማዘጋጃ ቤቶች ማለፊያ መነሻ ነጥቦች ናቸው።

አክስት ሙንያ ይህ “ራስን ማስተማርን" የሚመለከት እንደሁ ሲያስገነዝቡ፤

“በተቻለዎት መጠን ይማሩ፣ ይሳተፉ፣ በተለይም ከነባር ዜጎች ጋር። ፍርሃት ሊያድርብዎት አይገባም፣ ራስዎን ያስተዋውቁ፣ ወደ ማኅበረሰብ ኩነቶች ይዝለቁ” ይላሉ።

ነባር ዜጎችን ለማወቅ የመጀመሪያውን እርምጃ ጎብዞ የመራመድ ጉዳይ ነው።

Share