የበዓል ማዕድ ሳህንዎ ላይ ቡሽ ታከር የሚያቀርቡበት አምስት መንገዶች

Woman holding native Australian Lilly Pilly fruit.

A woman holding a harvest of native Australian lilly pilly fruit which is a nutritious form of bush tucker. Source: iStockphoto / Charlie Blacker/Getty Images/iStockphoto

Get the SBS Audio app

Other ways to listen

የአውስትራሊያን አገር በቀል ንጥረ ነገሮች ወደ መጠጥና ምግብ በማዋደድ የበዓል አከባበርዎን ወቅት ልዩ ያድርጉ።


አንኳሮች
  • ቡሽ ታከር "የጫካ ምግብ" የአውስትራሊያ አገር በቀል ምግብ ነው፤ በፕሮቲንና ፋይበር የተመጣጠነ መደበኛ ምግብ የተመላ ነው።
  • ቡሽ ታከርን ከግምት ውስጥ ሲያስገቡ ከደቡባዊ ንፍቀ ክበብ በጋ ጋር ተመሳሳይነት ያለው ምን እንደሁ ያስቡ፤ አንድ ተጠባቢ ያስረዳሉ።
  • አገር በቀሉ ንጥረ ነገር ከየት እንደመጣ ውይይት ለማካሔድ የአውስትራሊያ ነባር ዜጎችን የክብር ጉብኝት ማድረግ አንዱ መንገድ ነው።
ቡሽ ታከር አውስትራሊያ በቀል ምግብ ሲሆን በነባር ዜጎች የመበላት ታሪካዊነት ያለውና በርካቶችም በመመገብ እርካታ የሚያገኙበት ነው።

በአብዛኛው ቡሽ ታከር በፕሮቲኖችና ፋይበሮች ንጠረ ነገር የታጨቀ ነው፤ የተለያዩ ፍራፍሬዎች፣ ተክሎች፣ እንሰሳትና ዘሮችን ያካትታል።

በቅርብ ዓመታት ውስጥ አገር በቀል ንጠረ ነገሮች የሚያገኙት የትኩረት መጠን እየጨመረ ነው፤ ቤት ውስጥ ለማብሰል፤ ከየት ጀምሮ፤ መቼ አቀላቅሎ ወደ ምግብነት መለወጥ እንደሚገባ ለማወቅ አዋኪ ሊሆን ይችላል።

ዳሚየን ኮልትሃርድ፤ የፍሊንደርስ ሬንጀርስ አገር በቀል ንጥረ ነገሮችን የሚሸጠው ንግድ ተባባሪ መሥራች፣ የአድንያማታህና እና ዲሪ ሰው ነው።
RX015-Guests-CreditJiwonKim-TheCookUpS5-2023-04-27-4.jpg
Co-founder of Warndu, Damien Coulthard. Credit: Jiwon Kim Credit: Jiwon Kim
የቡሽ ታከር ምግብን አዋድዶ ለማብሰል ፍለጋና ምርምር አስፈላጊ ነው።

አቶ ኮልትሃርድ "በመጨረሻም፤ ልናበረታታ የምንሻው ምንድነው ሙከራን ከተለያዩ አገር በቀሎች ጋር በማዋደድ በሚያበስሉት ምግብ መደሰትን ነው" ብለዋል።

ለመጀመርም የተለያዩ ምግቦች ከሚቀርቡበት የበዓል ቀን የተሻለ ጊዜም እንደሌለ ያምናል።

ቡሽ ታከርን ከበዓላትዎ ጋር ሊያዛንቋቸው የሚችሉባቸው አምስት ነገሮችን እነሆ።

1. አገር በቀል ንጥረ ነገሮችን ሰላጣዎች ላይ ይጨምሩ

የአገር በቀል ንጥረ ነገሮች የምግብ አሠራር መመሪያን በመጠቀም ከመጀመር ይልቅ፤ ዝም ብለው በመደበኛ ንጥረ ነገሮች ይተኳቸው በማለትም አቶ ኮልትሃርድ ምክራቸውን ይለግሳሉ።

"በተለያዩ የጣዕም መገለጫዎች ውስጥ መሥራት ማለት ነው" ሲሉም ይናገራሉ።

ለምሳሌ ያህል፤ ዋሪጋል ግሪንስ ከስፒናች ጋር ሊዛነቅ ይችላል፤ ሳምፊር ከአስፓራገስ ጋር ሊዋደድ፤ እንዲሁም ሌመን ማይርትል ጠንካራ ግና ከሎሚ ጋር ተመሳሳይነት ያለው የሲትረስ ጣዕም ይሰጥዎታል።

2. ወቅትና አገር በቀል ነጥረ ነገሮችን ማብላላት

ተርኪ፣ ዶሮ፣ በግ ወይም ዓሣን አዘጋጅቶ ለማቅረብ፤ ፣ ለስቲር ፍራይድ ሌላው ቀርቶ ለ እንኳ ማለፊያ የሆነውን፣ ጨዋማና ከዕፅዋት የተቀመመ ጣዕም ያለውን የጫካ ጨው አክሎ ከአገር በቀል አማራጮች ጋር ወቅቱን ያጢኑ።

ፒፐርቤሪ ድንቅ ሊሠራ የሚችል ሲሆን፤ ጄራልድተን ዋክስ የሎሚ ፓይን ጣዕም አለው፤ እናም የባሕር ምግቦች ለማቆየት በጣሙን ተመራጭ ነው።

3. የባሕር ምግብን ይጠቀሙ

የሚኒዩንባል ሴት አራቤላ ዳግላስ ግንኙነቶችን በባሕላዊ ተዋድዶ የሚያቀናጀው ግንባር ቀደሙ የነባር ዜጎች ድርጅት የከሪ አገር መሥራች ናቸው።

አገር በቀል ንጥረ ነገሮች ሲታከሉ ከግምት ውስጥ ሊገቡ ስለሚገቡ ነገሮች ሲያስረዱ፤ ከደቡባዊ ንፍቀ ክበብ በጋ ጋር ሊስማሙ የሚችለት የትኞቹ ይሆኑ? ብሎ መጠየቅን ነው።

"የት እንዳለን ማስታወስና እንዳለንበት ሥፍራ መተግበር ይገባናል፤ ያለነው ደቡባዊ ንፍቀ ክበብ አኅጉር ነው" ይላሉ ወ/ሮ ዳግላስ።
RX013-Guests-CreditJiwonKim-TheCookUpS5-2023-04-24-5.jpg
Arabella Douglas is a founder of Currie Country. Credit: Jiwon Kim
"ማንም ሰው ከነባር ዜጎች አተያይ አኳያ አገር በቀል ወይም ባሕላዊ ገና ምንድነው ብሎ ሊለኝ ካሻ ፤ ይህ በወርኃ ዲሴምበር ወቅት ለእዚህ አኅጉር ኢኮሎጂያዊ እውነታ ምንድነው ከማለት ያለፈ አይሆንም" ይላሉ።

ወ/ሮ ዳግላስ ፕሮን እና የባሕር ምግብ ማለፊያ አማራጭ ሲሆኑ፤ ፒፒስ እና ሸርጣን ግና በእሳቸው ዘንድ ተወዳጆች ናቸው።

"ምስጢሩ በእጅ ያለውን ከማጣፈጡ ላይ ነው።

"በጣም ጠቃሚ የሆነን ነጥረ ነገር በአገር በቀል ንጥረ ነገር ሊተኩ እንደሚችሉ በጣሙን እንገነዘባለን" ብለዋል።

4. አገር በቀል ንጥረ ነገሮችን ዝነኛው ፓቭሎቫ ላይ ያክሉ

Strawberry Gum Pavlova with Wattleseed cream.jpg
Strawberry gum Pavlova with wattleseed cream. Credit: Josh Geelan and Luisa Brimble
ፓቭሎቫ አውስትራሊያ ውስጥ በበዓላት ሰሞን ከመደበኛ ምግብ በኋላ የሚቀርብ ኬክ መሰል ጣፋጭ ነው፤ ከአገር በቀል ንጥረ ነገሮችን ጋር አቀላቅሎ መሥራቱ ማለፊያ ነው።

"ሁሉም ሰው የእኛን ይወዳል፤ ክሪሙ ከዎትልሲድ ጋር የተቀላቀለ ነው" ይላሉ አቶ ኮልትሃርድ።

እንደ ኮንዶንግ፣ ዴቪድሰን ፕላምስና ማንትሪስ ከመሳሰሉ አገር በቀል ፍራፍሬዎች ጋር ሲቀርብ ደግሞ ከቶውንም መልካም ይሆናል ሲሉም አክለዋል።

በተመሳሳይ መልኩም ለበዓል ሰሞን ተወዳጅ እንደሆነው ትራይፍል ላይ አገር በቀሎቹን ፍራፍሬዎች መጨመር ይቻላል።

5. መጠጦችዎ ላይ አገር በቀል ንጥረ ነገሮችን ያክሉ

ዎትልሲ ያለ ካፊን ከተመሳሳይ ኃይል ሰጪነት ጋር ማለፊያ የቡና አማራጭ መሆን ይችላል።

ፊንገር ላይምስ እና ዴቪድሰን ፕላምስ መልካም ተቀባይነት ያላቸው ተጨማሪ ለስላሳ መጠጦች፤ ሌመን ማይርትል መልካም ከቶኒክ ጋር የሚቀላቀሉ መጠጦች አጋር መሆን ይችላሉ።

ሪቨር ሚንት እና አንት ሉዝ ሻይ የእርጋታ ስሜትን ሊቸርዎት ይችላሉ።

የማስታወሻ ማስፈሪያ ሰሌዳ ይፍጠሩና ያጋሩ

አገር በቀል ንጥረ ነገሮች ከየት እንደመጡ በተመለከተ ምርምርና ውይይትን መከወን አንዱ የአውስትራሊያን የበለፀገ ቅርስ ማክበሪያ መንገድ ይሆናል።

አቶ ኮርትሃርድ "ክፍለ አገራትን የመለየት ጥረት ያድርጉ፣ ከነባር ዜጎች ሕዝብ ጋር የተያያዙ የቋንቋ ስያሜንና የታሪክ ማስታወሻ ማሥፈሪያ ሰሌዳን በማዳበር እውነተኛ ማክበሪያ ያድርጉት"

"ያ እርስዎ ስለሚመገቡት እውነተኛ አድናቆትን ይቸርዎታል" ብለዋል።

Share