የአውስትራሊያ የቡና ባሕል ሲገለጥ

Serving coffee

How do you take your coffee? Australia’s coffee culture explained. (Getty) Credit: xavierarnau/Getty Images

Get the SBS Audio app

Other ways to listen

አውስትራሊያውያን አቅላቸው ለቡና የማለለ ነው፤ ተዘውትሮም ሜልበርን የዓለም የቡና መዲና በሚል ተቀጥላ ትጠቀሳለች። ቡናዎን በውል ማዘዝም ሁነኛ ጉዳይ ነው፤ ልክ ቡናን በማጣጣም ክህሎት እንደተላበሰ ባለሙያ ቡናዎን እንዘዝልዎት።


በየዕለቱ ቡና ይጠጣሉ። የደም ሥራችን ነው።

የአውስትራሊያ የቡና ባሕል ምዕራብ አውሮፓውያን ፍልሰተኞች ከእስፕሬሶ ማሺናቸው ጋር ቡናን አጣጥሞ የማድነቅ ልማዳቸውን ይዘው ከመጡበት አንስቶ ነው።

የእስፕሬሶ ማሺን ከፍተኛ ግፊ በማድረግ አንድ ላይ ተከማችቶ ያለውን ቡና ማለቂያ የለሽ የቡና ዘዬ ለመፍጠር ጨምቆ ያወጣል። በማያስገርም መልኩ በርካታ የቡና ስያሜዎች ምንጫቸው ጣሊያንኛ ነው።

ለዓመታት እስፕሬሶ (አጭር / ወፍራም ጥቁር ቡና) ከመጠጣት የተነሳ የላቀ ጥራት ያለው የቡና ፍሬን መሻት ይዘናል፤ ከመላው ዓለም እናስመጣና የአቆላልና አፈላል ቴክኒኮችን ሙከራን እናካሂዳለን።

የማፕ ቡና ባለቤት፤ ሳንቶ ቡቼሪ፤ እስፕሬሶ ወይም አጭር / ወፍራም ጥቁር ቡና በመባል የሚታወቀው የአብዛኛው ቡና መሠረትን የያዘና እውነተኛ የቡና ጣዕም ምን እንደሆነ ማለፊያ መግለጫ ነው በማለት ይናገራሉ።

አስደናቂ ሳይነስ ነው፤ አንድ ጥሩ ቡና አስተናጋጅ የእስፕሬሶ ማሽንን አጠቃቀም በግሩም ሁኔታ መከወን ይችላል።
እስፕሬሶ ወይም አጭር /ወፍራም ጥቁር ቡና፤ ከ 10–12 ግራም ያህል የተፈጨ ቡናና 30 ሚሊ ግራም ፈሳሽ ተጨምቆ የሚወጣ ነው።
ሳንቶ ቡቼሪ፤ ማፕ ቡና
አክለውም "ከተመሳሳይ የቡና ዱቄት መጠን በመጠቀም 20 ሚሊ ግራም ያህል ከሆነ ፈሳሽ ተጨምቆ ከሚወጣው ሪስትሬቶ (ristretto) ጋር አያምታቱት" በማለትም ልብ ያሰኛሉ።

ስለምን፤ በይበልጥ ወፍራም ነውና፤ ሪስትሬቶ ከእስፕሬሶ የበለጠ ጠንካራ ጣዕም አለው። ይሁንና እስፕሬሶ አንድ ነጠላ የቡና ቅጂ ሲሆን፤ በርካታ ቡና ቤቶች ሁለት ቅጂ በአንድ ሲኒ አክለው እንደሚያቀርቡም ልብ ይበሉ።
Brewing Espresso with Coffee Machine
The long black and latte are Australia’s most popular black and white coffees. (Getty) Source: iStockphoto / Tim Allen/Getty Images
ጥቂት ያለ ወተት የሚቀርቡ ዝነኛ ቡናዎችን እነሆ።

ጥቁር ቡናዎች

የሜልበርን የቡና ተጠባቢ ቡና ሱቅ ሥራ አስኪያጅ ሊሊ ፌይርሆል፤ ከእሳቸው ተሞክሮ አኳያ በጣሙን ዝነኛ ቡና ረጅም ጥቁር ቡና (ሁለት ዙር ቅጂ እስፕሬሶ በአንድ ሲኒ) እንደሁ ይናገራሉ።

አያይዘውም "ረጅም ጥቁር ቡና ሙቅ ውኃና ባናቱ ላይ ሁለት ዙር እስፕሬሶ የታከለበት ነው"

"እንዲሁም አጭር ጥቁር ቡና፤ ማለትም ነጠላ እስፕሬሶ ማግኘትም ይችላሉ። ያ በጣሙን የቡናን ጣዕም ለሚወዱ ወይም ካፌይን ፈጥኖ ውስጣቸው እንዲዘልቅ ለሚሹ ሰዎች የሚሆን ነው" ብለዋል።

እስፕሬሶን አሌ የሚያሰኝ ዝናን በማትረፍ ላይ ያለ አንድ ጥቁር ቡና አለ። የተጣራ ቡና ወይም በትልቅ ቡና ማፍያ "ጀበና" በጥንታዊ የአፈላል ዘዴ ተፈልቶ የሚቀዳ፤ ግና በጣሙን የተሻሻለ ጣዕም ያለው ነው።

ነጭ ቡናዎች

ነጭ ቡናዎች እስፕሬሶን መሠረት አድርገው ለብ ያለ ባለ አረፋ ወተት የታከለባቸው ናቸው።

ከእነሱ ውስጥ በጣሙን ዝነኛው ልስልስ ዓይን ሳቢ ባለ አረፋ ወተት ታክሎበት የጠርሙስ አካል ባለው ሲኒ የሚቀርበው ካፌ ላቴ (ወይም ላቴ) ነው።

ሌላውን ከላቴ ያነሰ ወተት በመያዝ ዓለም ላይ የተንሠራፋውና ምንጩ አውስትራሊያ ስለሆነው ልሙጥ ነጭ (flat white) ቡና ሊሊ ፌይርሆል ሲያመላክቱ፤

"ከሚቀርብበት ሲኒ ባስተቀር፤ በላቴና ልሙጥ ወተት ቡናዎች መካከል ልዩነት አለ ብዬ አላስብም" ብለዋል።

የጣፋጭ ፍቅር ካለብዎት፤ የወተት አረፋ ታክሎበትና የቸኮሌት ዱቄት ተነስንሶበት የሚቀርበውን ካፑቺኖ ይዘዙ።
Cappuccino art
Cappuccino art. Credit: pixelfit/Getty Images
ፒኮሎ ላቴ (piccolo latte - ትንሿ ላቴ) አነስተኛዋ ግና ጠንካራ ጣዕም ያላት ላቴ ናት። አንድ የእስፕሬሶ ቅጂ ከአነስተኛ ምጥን ወተት ጋር የያዘች ናት።

ሜልበርን ከፒኮሎ ላቴ ጋር ተመሳሳይ ሆኖ ጠንካራ በሆነውና ካፌይኑ ፈጥኖ ሰውነት ውስጥ በሚዘልቀው ሁነኛ ቡናዋ ትኩራራለች። ወተቱ ከላቴ አነስ ያለ፤ የጠንካራ ጣዕም ንፅፅሮሹ ዘነፍ ያለ ነው። በርካታ ሰዎች ያዝዙታል፤ አስማት ብለን ሰይመነዋል።

ማኪያቶ ጣዕሙን ለማለስለስ አረፋ የበዛት ወተት እስፕሬሶ ዝንቅ ነው።

ወ/ሮ ፌይርሆል ሲያስረዱ "ያንን የሚያዙት ካፌይኑ ፈጥኖ ሰውነታቸው ውስጥ እንዲዘልቅ የሚሹ ሰዎች ናቸው፤ ሆኖም የሙሉ ጥሬ እስፕሬሶ ጣዕምን አይሹም"

"ሚዛኑን ለማስጠበቅ ያህል የሚሹት ትንሽ የወተት ጠብታን ብቻ ነው" ይላሉ።

በአሁኑ ወቅት ቡና ቤቶች እንደ አኩሪ አተር፣ አጃ፣ ለውዝ የመሳሰሉ ከላም ወተት ነፃ የሆኑ ወተቶችን በአማራጭነት ያቀርባሉ፤ ይሁንና ለይተው የሚሹትን የወተት ዓይነት ካልተናገሩ በላም ወተት የተዘጋጀ የቡና ዓይነት ይቀርብልዎታል።
Two Smiling Colleagues Making Take Away Coffee Behind The Counter Of A Coffee Shop
Australians are coffee-obsessed, so much so that Melbourne is often called the world's coffee capital. (Getty) Credit: miniseries/Getty Images

ቡና ያለ ካፌይን

ወ/ሮ ፌይርሆል፤ ካፌይን አልባ ቡና ወይም 'decaf' ለረጅም ጊዜያት የቆየ ዝና አለው፤ ሆኖም ተገቢው አይደለም ይላሉ።
ለካፌይን አልባ (ዲካፍ) ቡና ጠጪዎች ከበሬታ አለኝ፤ ቡናን የሚጠጡት ለጣዕሙ ሲሉ ብቻ ነው። ቀኑን አንቅቶ እንዲያውላቸው አይደለም የሚጠጡት።
ሊሊ ፌይርሆል፤ የሜልበርን ቡና ተጠባቢ ሱቅ ሥራ አስኪያጅ
ካፌይን አልባ ቡና ባለፉት አሠርት ዓመታት ውስጥ በእጅጉ ተሻሽሏል። አሁን፤ በጣሙን ከፍተኛ ጥራት ካላቸው ጥሬ ቡናዎች ውስጥ አብዛኛውን ካፌይን ለይቶ በማውጣት ካፌይን አልባ (ዲካፍ) ቡና ብርቱ ተፎካካሪ ሆኗል።

ነጠላ ምንጭ ምንድን ነው?

የተወሰኑ ቡና ቤቶች ከአንድ ነጠላ ምንጭ ወይም ቅልቅል ምንጭ ካላቸው ቡናዎች መካከል ያስመርጣሉ። ቡና ወዳጆች ልዩ ተሞክሮ ለማግኘት ሲሉ ነጠላ ምንጭ ቡና ይጠጣሉ።

ሳንቶ ቡቼሪ "ነጠላ ምንጭ ከአንድ ቡና አቅራቢ ሀገር የመጣ ቡና ሲሆን፤ እንደ ቡና ሱቆቹ ቢለያይም፤ አልፎ አልፎ ቀጣናውን፤ ሲልም፤ አካባቢውንና የአምራቹን ስም ያስታውቃሉ፤ በጣሙን ማራኪ ነው"

"ቅልቅሉ የእነዚህ ምንጮች ዝንቅ ነው፤ እናም ዘላቂነት ይሰጥዎታል" ይላሉ።

አያሌ ምርጫ?

ከበርካታ አማራጮች ጋር፤ ቡና ቤቶች ምርጫዎችን ያቀርባሉ፤ ይሁንና የተወሰኑ ትዕዛዞች በጣሙን ብርቅዬዎች ስለመሆናቸው ሊሊ ፌይርሆል ሲናገሩ፤

"በቅርቡ አንድ የግማሽ ለውዝ እና የግማሽ አጃ ወተት ቅልቅል የቡና ትዕዛዝ ደረሰኝ፤ ያኔ 'ያንን ማድረግ አልችልም' ብዬ አልኩ። ስለምን፤ አንዳንዴ ብቃትን ግድ ይላል" ብለዋል።

ቤቢቺኖ (babycino)ን መዘንጋት የለብንም። ባንዲት ትንሽዬ ሲኒ የአረፋ ወተት ላይ የቸኮሌት ዱቄት የተነሰንሰበት ቤቢቺኖ የታለመው እኛ ቡናዎቻችንን ስንጠጣ ልጆች በእዚያ ላይ እንዲያተኩሩ ለማድረግ ነው። .

የተወሰኑ ሰዎች ያ ልጆችን ለሕይወት ዘመን ቡና ሱስ ለማዘጋጀት የተወጠነ ነው ብለው ያስባሉ። ጊዜ የሚፈታው ይሆናል።

Share