የነባር ዜጎች ሥነ ስዕል፤ ሀገራዊ ቁርኝትና የትናንት መስኮትነት

Lead Image.jpg

Gamilaraay/Bigambul and Yorta Yorta artist Arkeria Rose Armstrong Credit: Arkeria Rose

Get the SBS Audio app

Other ways to listen

ቃለ ልማዶችን ሞገስ በማላበስ፤ የአቦርጂናልና ቶረስ መሽመጥ ደሴት ሰዎች ሥነ ስዕልን ባሕላዊ ወጎቻቸውን፣ መንፈሳዊ እምነቶቻቸውንና ስለ መሬታቸው ያላቸውን መሠረታዊ ዕውቀቶች የማሸጋገሪያ ተግባቦት አድርገው ተጠቅመውበታል።


አንኳሮች
  • የነባር ዜጎች የሥነ ስዕል ሥራ ዝንቅ ነው፤ በነቁጥ ብቻ የተወሰነ አይደለም።
  • ሥነ ሰዕል እስከ ዛሬ ድረስ ባሕላዊ ወጎች፣ ሃይማኖታዊ እምነቶችና ዕውቀት ከትወልድ ወደ ትውልድ መተላለፊያ ተግባቦት ነው።
  • እኒህ የሥነ ስዕል ሥራዎች ሰዓሎዎች ከአገራቸው ጋር እንዲቆራኙ አጋዥ ነው።
  • የምልክቶች ትርጓሜ ገላጮቻቸው የሆኑቱ ሰዓሊዎች ፈንታ ነው።
የነባር ዜጎች ሥነ ስዕሎች መነሻው 17,500 ዓመታት የኋሊዮሽ ሔዶ ከሚነቅሰው በዓለም ዘመን ካሸመገሉትና በታሪክ ከበለፀጉቱ አንዱ ስለመሆናቸው ገንኖ ከሚገርላቸው ነው።

እኒህ የሥነ ስዕል ሥራዎች የአቦርጂናልና ቶረስ መሽመጥ ደሴት ሰዎች ባሕላዊ ወጎቻቸውን፣ መንፈሳዊ እምነቶቻቸውንና የምድርን አስፈላጊ ዕውቀት ሁነኛ ማሸጋገሪያ በመሆን አገልግለዋል።

የነባር ዜጎች ሥነ ስዕሎች የበለፀገ ዘርፈ ብዙ ጥበብን የያዙ፣ መጠነ ሰፊ ዘዬዎችናን ስልቶችን ያካተቱ፣ እያንዳንዳቸውም ከነባር ዜጎች ነጠላ ብሔር፣ ባሕልና ማኅበረሰብ ጋር በጥልቅ ሥር ሰድደው የተቆራኙ ናቸው።

ይሁንና፤ ብዙውን ጊዜ ሰዎች የነባር ዜጎችን ስዕል አስመልክቶ የተሳሳቱ ግንዛቤዎች እንዳላችው የዊራጁሪ ሰዎች የኩሪና 'ንፁህ ውኃ' ሴት ማሪያ ዋትሰን-ትራድጌት ያመላክታሉ።

የአቦርጂናል ታሪካቸውን ከፍ ባለ ስሜት ማጋራት የሚወዱት ወ/ሮ ዋትሰን-ትራድጌት የነባር ዜጎች አማካሪና ራሳቸውን በራሳቸው ያስተማሩ ሰዓሊ ናቸው።
MWT with artworks.JPG
Maria Watson-Trudgett is a First Nations consultant, a self-taught artist, and a storyteller Credit: Maria Watson-Trudgett Credit: Courtesy of Richmond Fellowship Queensland, 2019
“የተወሰኑ ሰዎች የነቁጥ ቅብ ልማዳዊና እውነተኛ የአቦርጂናል ሥነ ስዕል መለያ አድርገው ቀደም ብለው ውስጣቸው የሰረፁ ዕሳቤዎች አሏቸው። ይሁንና ጉዳዩ ይህ አይደለም፤ ዕሳቤው ጉድለትን የተላበሰ ነው።

“የእኛ ልማዳዊ ሥነ ስዕል ይበልጡን ቁሶች ላይ መለያዎችን ማሳረፍ፣ ዛፎችና የቀብር ሥፍራዎች ላይ መቅረፅ ወይም በኩነቶች ወቅት የሰውነት ቅብ ማድረግ ነው። የግድ ሥነ ስዕል መሆን የለበትም” በማለት ይገልጣሉ።

ወ/ሮ ዋትሰን-ትሩጌት በማከልም፤ የነቁጥ ቅብ የተጀመረው በቅርቡ በ1970ዎቹ የ ወቅት በአነስተኛ የሰሜን ምዕራብ አሊስ ስፕሪንግስ ነባር ዜጎች ማኅበረሰብ ነው። እዚህ ነበር የነባር ዜጎች ሰዓሊዎች ውኃ የተቀላቀለ ቀለም ቅቦችን ስስ ልሙጥ ቁሶች ላይ በማቅለም ልማዳዊ ወጎቻቸውን ማሳየት የጀመሩት ሲሉ ያስረዳሉ።
የነባር ዜጎች ሰዓሊዎችና ሥነ ስዕሎች ወጎቻቸውንና ባሕሎቻቸውን የሚያስተላልፉባቸው አያሌ ዘዬዎች አሉ። የነባር ዜጎች ሥነ ስዕል አንድ ነባር ዜጋ ከአገርና ባሕሉ ጋር የሚያስተሳስረውና ለፈጠራ የሚያበቃው ማናቸውም ዓይነት ቅብ ነው... ለእነሱ የቁርኝትና ተካታችነት መንፈስ ነው።
ማሪያ ዋትሰን-ትሩድጌት

ባሕልን ማጋራት

ወ/ሮ ዋትሰን-ትሩድጌት በ2009 ቅብ የጀመሩት ከሙሉ ቀን የዩኒቨርሲቲ ጫና ዘና መባያ መንገድ በማድረግ ነው። ይሁንና፤ ፈጥኖ ሥነ ስዕል "አዕምሮን ከማርጋት" ባሻገር የሚቸረው ትሩፋት ያለው መሆኑ ተገለጠላቸው።
ታሪኬን ከሌሎች ጋር የማጋራትና ባሕሌ ሕይወት ዘርቶ እንዲቀጥል ማድረግ ነው። እንዲሁም፤ ከነባር ዜጋ ባሕሌ፣ አገሬ፣ ከእኔ አረጋውያን ሰዎች ጋርና ከቤተሰቤ ጋር ካደግኩበት ቀዬ ከቀሰምኩት ዕውቀት ጋር እንድቆራኝ አጋዤ ነው።
ማሪያ ዋትሰን-ትሩድገት
የጋሚላሬይ / ቢጋምቡል እና ዮርታ ዮርታ ሰዓሊዋ አርኬሪያ ሮዝ አርምስትሮንግ፤ አያቶቻቸው ያጋሯቸውን ወጎች የሚያስታውሱት ፍቅር በተመላው ስሜት ነው።

የጋሚላሬይ አረጋዊቷ ሴት አያታቸው በቀጠናው የአሸዋ ቅብ ሰዓሊ ነበሩ።

“አሸዋማው መሬት ላይ ቁጭ ብላ ሳለች ወጓን ታወጋለች፤ ከአሸዋው ላይ ትተርክልናለች” ብለዋል።

አክለውም፤ ስለ ፈጠራ፣ እንሰሳት፣ ከዋክብትና የሴት ቅድመ አያታቸውን የአስተዳደግ ግለ ታሪክ አካትቶ፤ እኒህ ወጎች፣ ለትውልዶች እንደሚተላለፉና እያንዳንዱ ታሪክም የራሱ የሆነ አስተምህሮትን የያዘ መሆኑን ያስረዳሉ።
IMG_0580.jpg
Art has always been part of Arkeria Rose Armstrong’s life. Credit Arkeria Rose Armstrong
“የራሷን የሕይወት ጉዞና ታሪኮች በስዕል ሥራዎቿ ትገለጣለች። እናም፤ አያሌ ተምሳሌዎችና ምስሎች በእዚያ መልኩ ተጋርተዋል” ሲሉም ገልጠዋል።

ወ/ሮ አርምስትሮንግ የራሳቸውን የስዕል ሥራ የሚገልጡት "ሁለት አገሮቻቸው የተሳሰሩበት" ሲሉ ነው።

መንፈሳዊ መነቃቃትን ያገኙት ከሴት አያታቸው ተምሳሌቶችና ምስሎች ሲሆን፤ የሚጠቀሙበትን ቴክኒኮች ግና የወሰዱት ሰዓሊ ከሆኑት ወንድ አያታቸው ነው።

ወጎችን በስዕል ሥራዎቻቸው መልሶ ማውጋቱ ወ/ሮ አርምስትሮንግ ከሌሎቹ ጋር ያላቸውን ግንኙነቶች እንዲያንፀባርቁ ሲያስችላቸው፤ ለሴት ልጃቸውም በርካታ ውስጥን ፈንቃይ ስሜቶችን አጋርተዋል።
ባሕል እንዲቀጥል፤ ባሕልን ማጋራት ያሻል፤ ባሕል መተግበር ግድ ይላል። ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍም ወጎች ሲወጉ ሁሌም በጠረጴዛው ዙሪያ መኖራቸውን ማረጋገጥ መቻል አለብን።
አርከሪያ ሮዝ አርምስትሮንግ

ባሕላዊ ትስስሮሽ

ዳቪንደር ሃርት ሰዓሊ ናቸው፤ የቤተሰባቸው ሥረ መሠረት ከኑንጋር ብሔር ደቡብ ምዕራብ ቀጣና ምዕራብ አውስትራሊያ ነው። በጉልምስና ዕድሜያቸው ኒው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ ከንጌምባ ብሔር ባሕል ጋር ከመተሳሰራቸው በፊት የልጅነት ጊዜያቸውን ያሳለፉት አደላይድ ነው።

አቶ ሃርት በልጅነታቸው ወቅት ብርቱ ፈተናዎች የገጠሟቸው በመሆኑ ትምህርታቸውን በ16 ዓመታቸው አቋርጠዋል፤ ሥራ ለማግኘት ተቸግረዋል፤ ለአደንዛዥ ዕፅ ሱስ ተዳርገዋል።

ሆኖም፤ የአጎቶቻቸውና ወንድሞቻቸው ድጋፍ ሕወታቸውን ለመለወጥና ከባሕላቸው ጋር ለዳግም ትስስሮሽ አብቅቷቸዋል። ያም በአብዛኛው በስዕል ሥራዎቻቸው ላይ ይንፀባረቃል።

“በመልካም መንገድ እራስን እንደምን ማረቅ እንደሚቻል፣ ስለ ሀገር ቤት ወጎች ያስተማሩኝን አጎቶቼንና ወንድሞቼን ለማግኘት የታደልኩ ነበርኩ” ብለዋል።

ለአቶ ሃርት፤ ስዕል ከባሕላቸው ጋር መተሳሳሪያ መንገድ ብቻ ሳይሆን የመፈወሻ መንገድም ጭምር ነው።

“በትክክል፤ የቅብ ስዕል ስስል ውስጤ ይዘናል። አብዛኛውን ጊዜ መንፈስ የቅብ ሥራውን ይወርስና ቅቡ በራሱ ይከናወናል ብዬ አስባለሁ። በጣሙን ፈዋሽ ነው” ብለዋል።
IMG_20231021_143030_105.jpg
Davinder Hart at Saudi Arabia, UN gala dinner, 2023. Credit Davinder Hart

የጋራ ትርክት አካል ይሁኑ

ወ/ሮ ዋትሰን-ትሩድጌት የነባር ዜጎች ሰዓሊዎች ዘርፈ ብዙ ምልክቶችን በሥራዎቻቸው ውስጥ ሊያካትቱ እንደሚችሉ፤ የተወሰኑትም በተለይ እንደ እንሰሳት ፈለግ የመሰሉ የራሳቸውን ብሔር አንፀባራቂ እንደሚሆኑ ያመላክታሉ።

በሥራዎቻቸው ውስጥ የሚንፀባረቁት የሚቀጥሉት መስመሮችና የነባር ዜጎች ምልክቶች ቅድመ አያቶቻቸው መሬት ላይ ምልክቶችንና ምናባዊ ምስሎችን በመሳል እንደምን መልዕክቶችን ይለዋወጡ እንደነበር ያጣቅሳል።

የተወሰኑ ምልክቶች ሉላዊ ሊሆኑ ቢችሉም፤ ሌሎች ግና ለተለያዩ ሰዓሊዎች የተለያዩ ትርጉሞች ሊኖራቸው ይችላል።

“የምልክቶች ትርጓሜ እንደሚጠቀሙባቸው ሰዓሊዎች ይወሰናል። የምልክቶች አጠቃቀም በሌላ ሰዓሊ ዘንድም ተመሳሳይ ትርጉም አለው ብለው በጭራሽ አያስቡ” ሲሉም ግንዛቤ ያስጨብጣሉ።
ወ/ሮ አርምስትሮንግ፤ ትልቅ የመነሻ ሥፍራ የሚሆነው በሥነ ስዕል ዙሪያ ስለ ተነገሩ ወጎች መጠየቅ እንደሁ ያመላክታሉ።

“'ያ የነባር ዜጎች ሰው ማን ነው? እኒህ ብሔሮች እነማን ናቸው፤ ምን ይመስላሉ?' የሚሉ ጥያቄዎችን አንዴ መጠየቅ ከጀመሩ ያን ሰው ማየትና መረዳት ይጀምራሉ።

“የተወሰኑት የእኔ ተመራጭ መንገዶች የስዕል ሥራዎቼን በዐውደ ርዕይ በኩል ማጋራት ነው፤ እናም ቁጭ በማለት ከሰዎች ጋር ሆነው እኒያን የሥነ ስዕል ክሮች እየመዘዙ ማውጋት ይቻላል፤

“አንዳንድ ጊዜ በሥነ ስዕል ዕይታ ወቅት አነስተኛ ወግ አዘል ካርዶችን ማጋራቱ ውስኑነት ይኖረዋል ብዬ አስባለሁ። ወጎችን የምናጋራው ከሌላው ግለሰብ ጋር ባለን ግንኙነት መሠረት ይሆናል። እንደ ጋሚላሬይ ሴት፤ ወጋችንን የምናጋራው አንድ ሰው ለመማር ስንዱ ሲሆን ነው” ይላሉ።

ወ/ሮ ሃርት አክለውም “ግልፅ መሆን ነው፤ ጥያቄዎችን ለመጠየቅ ፍርሃት አይግባዎ፤

“እናም እዚያ ቦታ በእዚያ የሃሳብ ልውውጥ፤ ግንኙነቶችን እንገነባለን” ብለዋል።

Share