የነባር ዜጎች ፕሮቶኮሎች ለሁሉም አውስትራሊያውያን ጠቀሜታቸው እንደምን ነው?

Young Adult Indigenous Australian
Woman Dancing

Indigenous cultural protocols are based on ethical principles. Source: iStockphoto / chameleonseye/Getty Images/iStockphoto

Get the SBS Audio app

Other ways to listen

የአቦርጂናልና ቶረስ መሽመጥ ደሴተኛ ዜጎችን ባሕላዊ ፕሮቶኮሎች ልብ ብሎ መረዳት፤ ስለ ነባር ዜጎችና የምንኖርባት ምድር ግንዛቤ ለመጨበጥና ከበሬታን ለመቸር ጠቃሚ ወደፊት የመራመጃ እርምጃዎች ናቸው።


አንኳሮች
  • ባሕላዊ ሥነ ምግባር በአውስትራሊያውያን ነባር ዜጎች ዘንድ ሲተገበር በሺህዎች የሚቆጠሩ ዓመታት ተቆጥረዋል
  • የነባር ዜጎች አረጋውያን ባሕላዊ ዕውቀቶችን የተካኑና የሚያጋሩ፤ የተከበሩ የማኅበረሰብ አባላት ናቸው
  • በከበሬታ የተመሉ እስከሆነ ድረስ ጥያቄዎችን ለመጠየቅ ፍራቻ አይደርብዎ
  • አግባብነትና ጥንቃቄን የተላበሰ አባባልን መጠቀም ከበሬታን የማሳያ ቀላሉ መንገድ ነው
የነባር ዜጎች ባሕላዊ ፕሮቶኮሎች ከአቦርጂናልና ቶረስ መሽመጥ ደሴተኛ ሰዎች ጋር በሥራና በግል የሚኖሩንን ግንኙነቶች በሥነ ምግባራዊ መርሆዎች የሚያንፁ ናችው።

እኒህን ግንኙነቶች በመልካም ጎኑ መገንባት አስፈላጊ ነው፤ ስለምን የአውስትራሊያ ነባር ዜጎች ናቸውና። ከሥነ ምድር ጋር በፅኑዕ የተቆራኘ ዕውቀት ስላላቸው ስለ አካባቢ ጥበቃ ክብካቤ ሊያስተምሩን ይችላሉ።

ካሮላይን ሂዩስ፤ የአውስትራሊያ መዲና ግዛትና ቀጠና አረጋዊት ናቸው። እንደ ነባር ዜጋ አረጋዊትነታቸው ለጥልቅ ባሕላዊ ዕውቀት ከፍ ያለ ሥፍራ አላቸው።

“እኛ ከዓለም ጅማሮ አንስቶ...የእምነት ሥርዓቶችና ሥነ ምግባሮች አሉን። ያ እስከ ዘመናይቱ አውስትራሊያ ድረስ የሕይወታችን አካል ሆኖ አለ” ይላሉ።

ባሕላዊ ፕሮቶኮሎችን በመገንዘብ፣ ነባር ዜጎች ከመሬትና ልማዶቻቸው ጋር ላሏቸው ያልተቋረጠ ግንኙነት ዕውቅናን መቸር እንችላለን።
የSBS አረጋዊት ሮዳ ሮበርትስ ፤ የነባር ዜጎች ልማዳዊ ግብሮችን በመደገፉ ረገድ ገፍተውበት አሉ።

“አፈ ታሪኮችን፣ ፕሮቶኮሎችንና ሥርዓተ አምልኮዎችን ይህ ነው ለማይባል ጊዜ ቀጥለናል። ነገሮች እየተለወጡ ባለበት ሁነት፤ እኛ ቆሞ ቀር ሰዎች አይደለንም፤ የእኛ ማንነት መላ ቅድመ ሁኔታና ፍልስፍና ምድራችን፣ ባሕራችን፣ የውኃ መውረጃዎቻችንና ሰማይ የሆነውን ሀገራችንን መከባከብ ነው” ይላሉ።
AC Milan v AS Roma
Aboriginal dancers perform during the welcome to country before the friendly between AC Milan and AS Roma at Optus Stadium on May 31, 2024 in Perth, Australia. Credit: Paul Kane/Getty Images

ነባር አውስትራሊያውያንን የምንጠራው እንደምን ነው?

ካሮላይን ሂዩስ ‘አቦርጂናል’ ወይም ‘ቶረስ መሽመጥ ደሴተኛ’ በመላ አውስትራሊያ ተገቢ የሆነ አጠራር እንደሁ ይናገራሉ።

ሰዎች ራሳቸውን ከመጡበት ሥፍራ ጋር አቆራኝተው ማንነታቸውን ይገልጣሉ፤ ተዘውትሮ 'ኩሪ' ኒው ሳውዝ ዌይልስና ቪክቶሪያ ውስጥ 'ማሪ' ኩዊንስላንድ 'ፓላዋ' ታዝማኒያ ውስጥ ለመጠሪያነት ይውላል።

“የንጉናዋል ሴት ተብዬ መጠራቱን እመርጣለሁ፤ ስለምን የእኔ ብሔር ያ ነውና" በማለት ወ/ሮ ሂዩስ መለያቸውን ይጠቅሳሉ።
የእኔ ብሔር የቋንቋዬ ቡድንና የዘሬ ቡድን ነው፤ እናም ያ ለሌሎች የአቦርጂናል ሰዎች ከየት እንደመጣሁ ያመላክታቸዋል።
ካሮላይን ሂዩስ

ሁለት የተለያዩ የነባር ዜጋ ሰዎች

የቶረስ መሽመጥ ደሴተኞች በኬፕዮርክ ሰላጤ ጫፍና ፓፕዋ ኒው ጊኒ መካከል የሚገኙ የነባር ዜጎች ሰዎች ሲሆኑ፤ አብዛኛዎቹም የሜላኔዥያ ዝርያ ናቸው።

ቶማስ ማዮ የቶረስ መሽመጥ ደሴተኛና የአውስትራሊያ ማሪታይም ሠራተኞች ማኅበር ረዳት ብሔራዊ ፀሐፊ ናቸው። ነባር ዜጎች በእጅጉ ዝንቅ ስለመሆናቸው ይናገራሉ፤

“ሁሉም ነባር ዜጎች መጠነኛ ልዩነት ያለው ባሕሎች አሏቸው፤ ይሁንና በደሴተኛና አቦርጂናል ባሕል መካከል ግልፅ ልዩነት አለ። ደሴተኞች የተለዩ የነባር ዜጋ ሰዎች ሆነው መታወቅን ይወዳሉ” በማለት።
Both the Aboriginal and Torres Strait Islander flags are flown alongside the Australian national flag to acknowledge these distinct Indigenous peoples.
Both the Aboriginal and Torres Strait Islander flags are flown alongside the Australian national flag Source: AAP / AAP Image/Mick Tsikas

አክብሮት ያለው ቋንቋን መጠቀም

‘ነባሮች’፣ ‘አቦርጂናል’፣ ‘የቶረስ መሽመጥ ደሴተኛ’ እና ‘አረጋዊ/ት’ በዐቢይ ሆሄ መነሻውን የሚያደርግ ተገቢ ስሞች ናቸው። ምሕፃረ ቃሎች በእጅጉ ፀያፍ ተደርገው እንደሚወሰዱ ካሮላይን ሂዩስ ሲያስገነዝቡ፤

“በጭራሽ ‘አቦርጂናል’ የሚለውን በምሕፃረ ቃል አይጥሩ። እኛ ምሕፃረ ቃል አይደለንምና ያን አስመልክተን በጣሙን የተለየን ነን፤ ልቦቻችንን የሚጎዱ አፀያፊ ቃላቶችም አሉ” ብለዋል።

አረጋውያን እነማን ናቸው?

አረጋውያን ጥልቅ ባሕላዊ ዕውቀትን የተላበሱ የተከበሩ የማኅበረሰብ አባላት ናቸው። እንደ ‘አክስት’ እና ‘አጎት’ በሚሉ መጠሪያዎች ይጠራሉ። ነባር ዜጋ ላልሆኑ ሰዎች እኒህን መጠሪያዎች መጠቀም ይችሉ እንደሁ መጠየቁ ተገቢ ነው።

ኩነቶች በሚከናወኑበት ሥፍራዎች ወደ ሃገራችን እንኳን ደህና መጡ ሥነ ሥርዓቶች በአብዛኛው የሚከናወኑት በማኅበረሰብ አረጋውያን ነው።

‘እንኳን ወደ ሀገር ቤት መጡ’ ምንድን ነው?

አባባሉ የተሰየመው በ1980ዎቹ በሮዳ ሮበርትስ ነው። እንኳን ወደ ሀገር ቤት መጡ በኩነት መክፈቻ ወቅት ቀደምቶችን በክብር ለመዘከር የሚነገር ልማዳዊ ሥነ ሥርዓት ነው። ክንውኑም በንግግር፣ ዳንስ ወይም የጢስ ማጠን ሥነ ሥርዓት ሊሆን ይችላል።

በተመሳሳይ መልኩም ‘ሀገራዊ ዕውቅና’ በሁነኛ ስብስባዎች ወቅት በማንኛውም ሰው ሊነገር የሚችል የእንኳን ደህን መጡ ፕሮቶኮል መሆኑን ሮዳ ሮበርትስ ሲያስረዱ፤

“ዕውቅና እርስዎ የሚሠሩበት ወይም የሚኖሩበት ሥፍራ እርስዎ የመጡበት ሥፍራ ስላለመሆኑ ማረጋገጫ መስጠትና ይሁንታን መቸር ነው። እንዲያም ሆኖ፤ እርስዎ አንዱ አካል ነዎትና ለአረጋውያንና ባለቤቶችን ዕውቅናን ይቸራሉ” ብለዋል።
An Indigenous performer participates in a smoking ceremony.
An Indigenous performer participates in a smoking ceremony. Source: Getty / Cameron Spencer/Getty Images

አግባብ ያልሆነ ቋንቋ

ከሕፃናት ነጠቃ የሚመነጨው ቀደምት የመንፈስ ሁከት ሳቢያ፤ ሰዎች ለጥያቄዎች የሚሰጧቸው ምላሾች ላይ ተፅዕኖዎች እንዳሉት ካሮላይን ሂዩስ ሲናገሩ፤

“ስለ ፐርሰንቶች፣ ሌላው ቀርቶ የቆዳ፣ ዓይንና ፀጉር ቀለም መናገር በጣሙን አግባብነት ያለው አይደለም፤ ስለምን ልጆቻችንን ያሳደግነው በእዚያ መልኩ አይደለምና። ለእኛ በጣሙን የተለየ ነው። የነጭ ወይም ነባር ዜጎች ያልሆኑ ሕብረተሰብ ዘንድ እነዚህ ልጆች ተቀባይነት የላቸውም። በነባር ዜጎች ባሕል ዘንድ ግና እነዚህ ልጆች ለቤተሰቦቻችን፣ ለማኅበረሰባችን የመንፈሳዊ ዓለም ስጦታዎች ናቸው፤ እናም ሁሌም ተቀባይነት አላቸው” ይላሉ።

ተጨማሪ ዕውቅትን በመቅሰም ከበሬታዎን ያሳዩ

ቶማስ ማዮ፤ ፕሮቶኮሎችን አስመልክቶ ጥያቄዎችን ለመጠየቅ ፍራቻ አይደርብዎ፤ እውነተኛና የተከበረ ሥፍራ እንደ መጡ ሁሉ በማለት ሲያብራሩ፤

“እናም በጣሙን ጠቃሚ ነገር ማድመጥ፣ ማብራሪያዎችን መቀበልና በአክብሮት ወደፊት መራመድ ነው” ይላሉ።

አቶ ማዮ አክለውም፤ ተሰናድቶ ያለውን የኡሉሩ መግለጫ ሁሉም ሰው ከልብ እንዲያነብና ድጋፉንም እንዲቸር ያሳስባሉ።

የSBS አረጋዊት ፕሮቶኮሎች ሰብዓዊ ፍጡራንን ዕውቅና ለመቸር አሥፈላጊ መሆናቸውን ልብ ያሰኙናል።
ይህ ትህትናና ርሕራሔን የሚመለከት ነው፤ ማጠቃለያውም መልካም ሥነ ምግባር ነው።
ሮዳ ሮበርትስ
This content was first published in May 2022.

Share