ስፌት ለነባር ዜጎች ያለው አስፈላጊነት ምን ያህል ነው?

Australia Explained: First Nations weaving - Aboriginal craftswoman splitting pandanus for weaving

Ramingining, Arnhem Land, Northern Territory, Australia, 2005. Credit: Penny Tweedie/Getty Images

የእጅ ስፌት ውስብስብና ረቂቅ ከሆኑት የነባር ዜጎች ቴክኖሎጂና ባሕል ውስጥ አንዱ አብነት ነው። የውበት ቁሶችን ይፈጥራል፤ ሂደቱም ጥልቅ ባሕላዊ ፋይዳ አለው። የእጅ ስፌት ዕውቀትን የማጋሪያ መንገድ፣ ሰዎችን ከቀዬአቸው ጋር ማገናኛ፣ አስተውሎትን መጋበዣና ከዚያም ላቅ ያለ ነው።


Key Points
  • ስፌቶች ሰፊውን፣ ቀዬን፣ ቀደምት አባቶችንና እናቶችን አስተሳሳሪ ተዳሳሽ ቁሶች ናቸው
  • ስፌት ለማሕበራዊ ግንኙነት የአስተውሎት መሳሪያ ሆኖ ያገለግላል
  • የእጅ ስፌት ባለሙያዎች ሥራዎቻቸውን የሚያንፀባርቁ መለያዎች ይኖሯቸዋል
  • ሁለቱም ፆታዎች ወንዶችና ሴቶች የእጅ ስፌት ይሰፋሉ
የእጅ ስፌት ቁሶች እንደ ሰፌዎቹ ነባር ዜጎች ሁሉ ይለያያሉ። እያንዳንዱ ቁስ ከሰፊዎቹ ቀዬና ዝርያዎቻቸው ጋር ያለውን ተያያዥነት ጎልቶ የሚሳይ ጠቃሚ ቁስ ነው።

የእጅ ስፌቱ የሚጀምረው እንደ ሸምበቆዎች፣ ቅርፊትና ተክሎችን የመሳሰሉ መጠቀሚያዎችን በማሰባሰብ ነው።እኒህ ስፌቶች እንደ ቅርጫቶች፣ ጎድጓዳ ሳህኖች፣ ገመድና መረቦችን የመሳሰሉ ውስብስብ ሥርዓተ ጥለት ቁሳቁሶችን ለመፍጠር የሚሰፉ ናቸው።

የሰሜናዊ ኒው ሳውዝ ዌይልስ ጎሜሮይ ሴት፤ ሰዓሊና መምህርቷ ቼሪ ጆንሰን “ስፌት በእንግሊዝኛ አንድ ቃል ነው፤ በመጀመሪያ የእናት ቋንቋ ግና የተለያዩ ቃላቶች አሉት"

“የእጅ ስፌት ብለን የምንጠራው በዓመት ውስጥ በየትኛው ወቅት፣ የትኛው ዓይነት ተክል እንደሚነቀል፣ እንዲሁም ዘላቂነት ባለው መንገድ ለምግብነት የሚሰበሰብ ከቁሶቹ ጋር የተያያዘ ሁነኛ ባሕላዊ ዕውቀትን የያዘ ነው” ይላሉ።
AFLW Rd 8 - Yartapuulti v Gold Coast
ADELAIDE, AUSTRALIA: An Indigenous weaving workshop takes place in The Precinct Village an AFLW match. Credit: Kelly Barnes/AFL Photos/via Getty Images

የእጅ ስፌት ሰዎችን ያገናኛል

የእጅ ስፌት ስለ ስፌት መማርና ሂደቱ ብቻ አይደለም።

የተለያዩ ትውልዶች ታሪኮችን ለማውጋት በጋራ ተሰባስበው ተቀምጠዋል፤ ሰዎች ስለምን እንደሚሰፉም ባሕላዊ ዕውቀትን ቀስመዋል።

“ እንደ እውነቱ ከሆነ ጠቃሚው ነገር በምን እንደሚሰፉ፣ የሚሰፉት ቁስ ለምን አገልግሎት እንደዋለና እንደምን በአግባቡ ሊጠቀሙበት እንደሚችሉ መረዳት ነው። በርካታ ነገሮች የተሰናሰሉበት ነው” ሲሉ ወ/ሮ ጆንሰን ተናግረዋል።

አዎን – ወንዶችም ይሰፋሉ

ሉክ ራስል በኒው ሳውዝ ዌይልስ የኒውካስትል አካባቢ የዎሪሚ ጠባቂ ናቸው። ተግባራቸው አረጋውያኖቻቸው ባሕላዊ ታንኳዎችን መገንቢያ ቅርፊቶችን፣ የአሳ ማጥመጃ ጦሮችን መሥሪያና ስለ ሌሎችም ቁሳቁሶች ዕውቀቶችን መቅሰምና ማሸጋገርን ያካትታል።
ለእኔ፤ የእጅ ስፌት፣ በአብዛኛው፤ በተለይም የገመድ ግመዳ ቁሳቁሶች በእኛ ወንዶች ዘንድ ትልቅ ሚና ይጫወታሉ።
ሉክ ራስል፤ ባሕላዊ ዕውቀት ተከባካቢ
የታንኳዎችን ጫፎች ወይም ቁሶችን ከተገመዱ ገመዶች ጋር ለማያያዝ ረቂቅ የሆኑ የእጅ ስፌት ቴክኒኮችን ይጠቀማሉ።

ከባሕል አንፃር ወንዶች ከልጅነት እስከ ለጋ ወጣትነት ዓመታት፤ ከቤተሰቡ በተዋረድ በዕድሜ ከገፉ ሴት ጋር ጊዜያቸውን ያሳልፋሉ እንዲሁም ከልጃገረዶች ጋር ጎን ለጎን ተቀምጠው የእጅ ስፌት ይማራሉ።

“ለወጣት ወንድ ልጅ፤ በተለይም ከታዳጊ ልጅነት ወደ ጉልምስና እያመራ ያለ፤ ክህሎቶቹን የሚጠቀመው በእዚህ ወቅት ነው”

“እናም እስከዚያ ደረጃ ድረስ የቀሰማቸውን ክህሎቶች ሁሉ ያስተማሩት ሴቶች ናቸው” ይላሉ አቶ ራስል።
Australia Explained: First Nations weaving -  pandanus palm fibre mats
Credit: Richard I'Anson/Getty Images

ስፌት እንደ ማሰላሰያ

ቼሪ ጆንሰን የእጅ ስፌትን ምናባዊ ሃሳባቸውን እንደማስፈሪያ ይጠቀመቡታል። ከአስተውሎት ጋር በመስፋትም ዕሳቤዎቻቸውን ከቁሱ ጋር ያዋድዱታል።

“የእኛ ማኅበረሰብ ነገሮችን የሚያካሂዱት እንዲያ ነው”

“በጋራ ሆነን በፍቅርና እንደ ቤተሰብ እውነተኛ መከባበር በተመላበት መንገድ እንከውናለን፤ የእጅ ስፌት ክዋኔ እንዲያ ነው። ሰዎች በጋራ ተሰባስበው እንዲሰፉ ያደርጋል። አንዳንዴም በእኛ የስፌት ክቦሽ ውስጥ ያሉ ሰዎች ከሌሎች እህቶች ጋር አብሮ ለመሆንና ሻይ ለመጠጣት ይመጣሉ” ይላሉ።

የዘይቤ ልዩነቶች

እንድ ሳሮችና ቅርፊትቶች ያሉ የተክል ምንጮች በመላ አገሪቱ የተለያዩ ናቸው፤ እናም ከቀጣና ቀጣና የስፌት ዘይቤዎችም ይለያያሉ።

ይሁንና ሰፊዎች የየራሳቸው ቅልጥፍናና የሚለዩባቸው ዘይቤ አሏቸው።

አንዱ መንገድ የአካባቢውን አበቦች፣ ቅርፊቶች፣ ጭማቂዎች ወይም ስሮች መጠቀም ነው።

ቼሪ ጆንሰን “አንድ የጥበብ ሰው ሆን ብሎ የሚጠቀምባቸው የአበባ ቀለማት እንደ እውነቱ ለግለሰቡም ለአካባቢውም ፋይዳ አለው” ይላሉ።
በተለምዶ አንድ የተካነ ዓይነት ያለው ሰው ስፌቱ ከየትኛው ቀጣና እንደሁ ለይቶ ማወቅ ይችላል፤ አንዳንዴም ባለሙያውን በቀለማቱ፣ በዘዬው፣ በአሰፋፉና በተጠቀመባቸው ቁሳቁሶች ሊለይ ይችላል።
ቼሪ ጆንሰን፤ አርቲስትና መምህርት
አንዳንዴ የእጅ ስፌቱን መሠረት በመመልከት አርቲስቱን መለየት ይቻላል።

አርቲስት ኔፊ ዴንሃም በሰሜናዊ ኩዊንስላንድ ካርድዌል የጊራሜይ ባሕላዊ ባለቤት ናቸው። ስፌት ያስተማሯቸው አጎታቸው ናቸው።

“እኔን ጨምሮ በርካታዎቹ የእኛ አርቲስቶች፤ የእጅ ስፌት የጀመርነው በተለያየ መንገድ ነው"

“እንዲያ በመሆኑ ነው መሠረቱን በመመልከት የግራ ይሁን ወይም የቀኝ ስፌት መሆኑን መናገር የሚቻለው። እናም ማን እንደሠራውም መናገር ይቻላል” ሲሉ ዴንሃም ይናገራሉ።

Australia Explained: First Nations weaving - Woman weaving basket with pandanus palm fibre
Credit: Richard I'Anson/Getty Images

ተሳትፎ ማድረግ እንችላለን?

ካሲ ሊትሃም፤ ቪክቶሪያ ውስጥ የኩሊን አገር ታዩንጉራንግ ሰው ሲሆኑ፤ ዘርፈብዙ አርቲስትና በእጅጉ የተጠበቡ ሰፊ ናቸው። ነባር ዜጎች ላልሆኑ ሰዎች ክፍት የሆኑና በነባር ዜጎች የሚመሩ ሆርሻዎችን አስተባብረዋል።

ተሳታፊዎች የነባር ዜጎች ሰፊዎች አመጣጥ ከየት እንደሆነና ከቅድመ አያቶቻቸውና እናቶቻቸው ጋር ስላሏቸው ግንኙነቶች በውል ተረድተው እንዲያስተዋውቁ በተመስጦ እንዲያደዳምጡ ይበረታታሉ።

ወ/ሮ ሊትሃም “እኒህ ሆርሻዎች የሚካሔዱት በነባር ዜጎች እንደሁ ማወቃቸው ጠቃሚ ነው፤ የእኛን አውስትራሊያ ውስጥ የባሕላዊ ዕውቀት የአዕምሮ ንብረት ባለቤትነት ጠቀሜታን ሊገነዘቡ ይገባል” ብለዋል።

ይህ ፕሮቶኮልን የመገንዘብ ጉዳይ ነው። ሁላችንም የተማርናቸውን መጋራት እንችላለን፤ ይሁንና ትርፍ ልናገኝበት አይገባም፤ ሁሌም ለነባር ዜጎች መምህራኖቻችን ዕውቅናን ልንቸር ይገባናል።

ለሁሉም ክፍት የሆኑና በነባር ዜጎች የእጅ ስፌት ሰፊዎች ማኅበረሰባት የሚመሩ ፌስቲቫሎችን ፈልገው ማግኘት ይችላሉ። ሆርሻዎች ተዘውትረው በአካባቢ ማዘጋጃ ቤቶች በማኅበራዊ ሚዲያና ሰው በሰው ይተዋወቃሉ።

የዋነኛ ማኅበረሰብ ታይታ

የእጅ ስፌቶች ለዕይታ ይቀርባሉ፤ በአነስተኛና ትላልቅ የምስላት ማዕከል ውስጥም በመላ አውስትራሊያ በግልና በሕዝብ መታደሚያዎች፤ ሌላው ቀርቶ በፋሽን ማሳያ ሥፍራዎች ይሸጣሉ።

የምስላት ማዕከል የነባር ዜጎች ባሕሎችንና አካባቢዎችን ዝንቅነት ለታይታ ማብቃት ጠቃሚ ነው።

“እንደ እውነቱ ከሆነ ዛሬ አሁነኛ የሆነውንና ያለፈውን ዋነኛ የእጅ ስፌት አስተውሎት ቸሮ የሚያሳይና ሁላችንም ሰፊ የሆንን ሁሉ ለወደፊቱ መጪ ትውልዶች የምንቀጥልበት ነው”

“እናም ሰዎች ወደ ምስላት ማዕከል ሲሄዱ፤ የእኛ እጅ ስፌት አውስራሊያ አቀፍ ስለ መሆኑ፤ እያንዳንዳቸውም በእጅ ስፌት ወይም ተዋድደው በተሰፉባቸው ቁሶች ፋይዳ ያለው ባሕላዊ ታሪክ ያላቸው መሆኑን ልብ ሊሉ ይገባል” ሲሉ ካሲ ሊትሃም ያሳስባሉ።

Share