የጡረታ ገንዘብዎን እንዴት ይጠብቁታል ፤ የጠፋ የጡረታ ተቀማጭን እንዴት ማግኘት ይቻላል ፤ በውጭ አገር መኖር ከፈለጉ ምን ማድረግ አለብዎ ?

Saving coins

Setting up an online account with your superannuation fund helps you track the mandatory contributions coming in from your employer. Credit: urbancow/Getty Images

Get the SBS Audio app

Other ways to listen

የጡረታ አበል ተቀማጭ አካሄድ ውስብስብ ሊሆን ይችላል ፤ ምንም እንኳ የጡረታ ተቀማጭዎ ባይንቀሳቀስም ገንዘብዎ እስከወዲያኛው እንደማይጠፋ ያውቃሉን ? የማስመለስ ሂደቱ ምን ይመስላል ? ወደ ውጭ ሀገር ቢሄዱ ወይ የጡረታው ባለቤት በሞት ቢለይ የጡረታው ገንዘቡ እንዴት ይሆናል ?


አንኳሮች
  • የጡረታ ገንዘብዎ እንዳይጠፋ አድራሻዎን ለአስቀማጭ ድርጅትዎም ሆነ ለአውስትራሊያ ታክስ ቢሮ በየጊዜው ማሳወቅ አለብዎት
  • የአውስትራሊያ ዜጎች እና ቋሚ የመኖርያ ፈቃድ ባለቤቶች ፤ የጡረታ ገንዘባቸውን ቀድሞ ማውጣት የሚፈቀድላቸው በጣም የተለያ ሁኔታ ውስጥ ካሉ ብቻ ነው
  • ከሞት በኋላ የጡረታ ገንዘብ ተቀማጭ ክፍፍልን በተመለከተ የሚነሱ የቤተሰብ ግጭቶችን የሚመለከተው ገለልተኛ አካል ነው
የጡረታ ገንዘብ ማለት ቀጣሪዎ በስራው አለም ወስጥ እያሉ የሚያስቀምጥልዎ ገንዘብ ሲሆን ጡረታ በሚወጡ ጊዜ ለመኖር የሚጠቀሙበት ገንዘብ ነው ።

ቀጣሪዎች የጡረታ ገንዘብን ለተቀጣሪዎች የማስቀመጥ ግዴታ ያለባቸው ሲሆን ፤ የጡረታውን ገንዘብም ድርጅቶቹ ግለሰቡ ጡረታ እስኪወጣ ድረስ ተጨማሪ ገቢ እንዲያመጣ ሲሰሩበት ይችላሉ።

አውስትራሊያውያን ለጡረታ ያሰቀመጡት ገንዘብ ሙሉ ለሙሉ እንዳይጠፋ የሚከላከል የተቀመጡ አካሄዶች አሉ ። የተቀማጭ ሂሳብዎ በተለያየ ምክንያት የማይንቀሳቀስ ቢሆንም ገንዘብዎ ግን በፍጹም አይጠፋም።

አድራሻዎትን ከቀየሩ እና የጡረታዎ ድርጅትዎ ሊያገኝዎ ካልቻለ ፤ ያልተጠየቀ የጡረታ ገንዘብ በሚል ለአውስትራሊያ ታክስ ቢሮ ይተላላፋል።

የጠፋ የጡረታ ገንዝብዎን ማስመለስ

የአውስትራሊያ ታክስ ቢሮ መረጃው ከደረሰው በኋላ ፤ የጠፋውን የጡረታ ገንዘብ ባለቤት ለማግኝት የተለያዩ ቅደመ ተከትሎችን ማለፍ ግድ ይለዋል ።
ነገር ግን እርስዎ የጠፋ የጡረታ ገንዘብ አለኝ ብለው የሚያስቡ ከሆነ ፤ ከአውስትራሊያ ታክስ ቢሮ በኦን ላይን አገልግሎት መፈለግ ጥሩ አማራጭ ነው ።

young asian couple using laptop to pay bill at home
There is no deadline for recovering unclaimed super, but the longer it sits held by the ATO, the longer you are missing out on investment returns. Credit: rudi_suardi/Getty Images
አድራሻ በቀየሩ ቁጥር ሁልጊዜም ማሳወቅ አስፈላጊ ነው።

“ ሰዎች ማድረግ የሚኖርባቸው የቀድሞ የጡረታ ድርጅቶቻቸውን በቀጥታ በማግኘት አድራሻቸው እና የባንክ ቁጥራቸው ትክክል መሆኑን ከአውስትራሊያ ታክስ ቢሮ ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል። ” የሚሉን ወ/ሪት ሮዝንስዌንግ ናቸው።

ዛቪየር ኦሆሎራን የሱፐር ኮንሲዩመር አውስትራሊያ ዳይሬክተር እና የገለልተኛ የጡረታ አበል ተጠቃሚዎች አስተባባሪ እንደሚሉት ፤ ከአንድ በላይ የጡረታ ተቀማጭ ሂሳብ መኖር ያልተለመደ አይደለም። ነገር ግን ይህ መሆኑን ካውቅን ሁሉንም ወደ አንድ ላይ ማጠቃለሉ የተሻለ አማራጭ ነው ።

Portrait of four factory staff smiling towards camera
When joining a new employer, they can set up your super account automatically with a fund if you don’t nominate yours. Credit: JohnnyGreig/Getty Images
በተለያየ ሂሳብ የጡረታ ገንዘብን ማስቀመጥ በግምት እስከ $50,000 የሚሆን የጡረታ ገንዘብን ያሳጣል ።
ዛቪየር ኦሆሎራን የሱፐር ኮንሲዩመር አውስትራሊያ ዳይሬክተር
ለጡረታው ገንዘብ መቀነስ ዋነኛው ምክንያቱም ከአንድ ቦታ በላይ የኢንሹራንስ ክፍያ ስለሚደረግ ነው ።

“ በእነዚህ የሂሳብ ማጠራቀሚያዎች የተገደቡ ክፍያዎች አሉ ፤ ስለዚህ ከአንድ በላይ የጡረታ ሂሳብ ማጠራቀሚያ ካለዎት ክፍያዎችን በእጥፍ እየከፈሉ ነው ማለት ነው ፡፡”

Adding up the profits
“It really does pay to keep on top of where your super is and consolidate where it's appropriate,” says Mr O’Halloran. Credit: djgunner/Getty Images
በጊዜያዊ የመኖሪያ ፈቃድ በአውስትራሊያ ስራን ሲሰሩ የነበሩ ፤ አገሪቱን ለቅቀው ከሄዱ በኋላ የጡረታ ገንዘባቸውን መጠየቅ ይችላሉ ።
በአውስትራሊያ እንዳሉ Departing Australia superannuation payment (DASP) የሚለውን ማመልከቻ መሙላት የሚችሉ ሲሆን ፤ ማመልከቻውን ማስገባት የሚችሉትም አገሪቱን ለቅቀው ከወጡ ፤ የመኖሪያ ፈቃድዎ ካለቀ እንዲሁም ከተሰረዘ በኋላ ነው።

“የመኖሪያ ፈቃድዎ ካለቀ እና ከአውስትራሊያ ከውጡ በስድስት ወር ውስጥ ይህንን ካላደረጉ፤ የጠፋ የጡረታ ገንዘብ ተብሎ ለአውስትራሊያ ታክስ ቢሮ ይተላለፋል ።” ሲሉ ወ/ሪት ሮዝንስዌንግ ይናገራሉ ።

" ገንዘቡ የእርስዎ ነው ፤ በማንኛውም ሰአት ሊጠይቁ ይችላሉ ፤ ነገር ግን እስከዚያው ድረስ የአውስትራሊያ ታክስ ቢሮ ይዞ ያቆየዋል ።፡"


Apple picking during harvest in a fruit orchard
Temporary visa residents can apply to have their super paid to them as a departing Australia superannuation payment (DASP) after leaving the country. Source: Moment RF / Robert Lang Photography/Getty Images
ቋሚ መኖሪያ ያላቸው እና የአውስትራሊያ ዜጎች በውጭ አገር ለመኖር ቢፈልጉ የጡረታ ገንዘባቸውን የሚያገኙት በመደበኛው አሰራርና አካሄድ ብቻ ነው ።

“ስለሆነም የጡረታ መቀበያ እድሜ ላይ መድረስ ግድ የሚል ሲሆን ፤ሌሎች ተጨማሪ ቅድመ ሁኔታዎችንም ማሟላት ግድ ይላል።

ምንም እንኳን ከአውስትራሊያ ለቅቀው ቢሄዱም የጡረታ ገንዘብዎን ለማግኝት ውሱን ከሆኑ ምክንያቶች ባሻገር በፍጹም ማግኘት አይችሉም ፤ ለምሳሌ ከፍተኛ የሆነ የገንዘብ ችግር ካጋጠመዎ ፤ወይም በሜዲኬር ሊሸፈን የማይችል የጤና ችግር ከገጠመ ብቻ ሊፈቀድልዎት ይችላል።

በውጭ አገር ሲኖሩ የጡረታዎትን ሁኔታ ይከታተሉ

እንደ አቶ ኦሆሎራን ምክር ከሆነ በውጭ ሀገር ሲኖሩ የጡረታ ገንዘብዎን በአግባቡ ለመቆጣጠር ፦

· አድራሻዎትን በየጊዜው በማሳወቅ የጠፋ የጡረታ ገንዘብ እንዳይባል መከላከል

· የጡረታ ገዘብዎን እንቅስቃሴ በየጊዜው ከአውስትራሊያ ታክስ ቢሮ , መከታተል

· የሚከፍሉት ኢንሹራንስ እርስዎ ከአገር ውጭ ሳሉ የሚሸፍንልዎት መሆኑን ማረጋገጥ

በተጨማሪም የማያስፈልጉ ክፍያዎችን እየከፈሉ መሆኑን ማጣራት ይኖርብዎታል።
Young woman holding suitcase or baggage with backpack in the international airport.
If you are an Australian citizen or permanent resident, moving overseas does not change the rules around how your superannuation is treated. Source: Moment RF / Mongkol Chuewong/Getty Images
አሁን ገበያው ላይ ባለው አሰራር ፤ የጡረታዎ ተቀማጭ $ 50,000 ያህል ከሆነ ፤የሚከፍሉት ክፍያ በአማካይ በአመት 1% መሆን አለበት ። ይሁን እና ከዚህ ያነሰን ክፍያን የሚያስከፍሉ በገበያው ውስጥ እንደሚኖሩ እሙን ነው ።

“ የገበያ ጥናትን ማድረግ እጅግ አስፈላጊ ሲሆን በዚህም አነስተኛ የሚባለውን ክፍያ እየከፈሉ መሆኑን ማረጋገጥ ይችላሉ ። በተጨማሪም በውጭ አገር ባሉበት ጊዜም ያጠራቀሙት ገንዘብ በክፍያዎች ብቻ ተሸርሽሮ አለማለቁን እርግጠኛ መሆን አልብዎት። “ ሲሉ አቶ ኦሆሎራን ይናገራሉ ።

" ምንም እንኳ በውጭ አገር እየኖሩ ቢሆንም ፤ የወደፊቱ የጡረታ ጊዜዎ ገንዘብ ተቀማጭ እንዲያድ ተጨማሪ ገንዘብን ማከል ይችላሉ ።"

ከህልፈት በሗላ የጡረታ ተጠቃሚዎች

ምንም እንኳ የጡረታ ተቀማጭ ገንዘብ ለእርስዎ ተብሎ የሚቀመጥ ቢሆንም ፤ ህይወት ካለፈ በሗላ የጡረታ ክፍያዎን ሊወስዱ ወይም ሊጠቀሙ የሚችሉ ሰዎችንም መወከል አስፈላጊ ነው ።

ከሞት በሗላ የጡረታ ገንዘብ ክፍፍል በተመለከተ የሚነሱ ቅሬታዎችን የሚያይ የተለየ አካል ያለ ሲሆን ይህውም (AFCA). በመባል ይታወቃል ።

ሂዘር ግሬይ የጡረታ ቅሬታ ሰሚ ተቋም መሪ እንደሚሉት ከሆነ በብዙ ሰዎች ዘንድ ያለው ግምት ገንዘቡ በቀጥታ ወደ እነሱ እንደሚሄድ ነው ።

ብዙ ሰዎች ካላቸው የቤተሰብ ቤት ቀጥሎ የጡረታ ገንዘባቸው ዋነኛ ቅርሳቸው ነው ። በአብዛኛውም ያላቸውን ሀብት ላይ ኑዛዜን የሚያደርጉ ሲሆን ፤ የጡረታ ገንዘባቸውን ለማከፋፈል ግን የባለሙያን ምክርን አይጠይቁም ።
ሂዘር ግሬይ የጡረታ ቅሬታ ሰሚ ተቋም መሪ AFCA
የጡረታ አስቀማጭ ተቋማት ከህልፈት በኋላ ያለውን ውርስ ተከትሎ ከወራሾች ጥያቄዎች ሲቀርቡላቸውም ፤ ክፍፍሉ ፍትሀዊ መሆኑን በተመለከተ ጥያቄ ያላቸውን ወራሾች ወይም ተጠቃሚዎች በ 28 ቀናት ውስጥ ወደ መምራት ይኖርባቸዋል።
Retired woman managing on a low income
If you don't make a written death benefit nomination, the trustee of your super fund will decide who receives your death benefit. Credit: Kemal Yildirim/Getty Images
ውሳኔው የሚገመገም ሲሆን ፤ በተነሳው ቅሬታ ላይ ተመስርቶም በጋራ የሚያስማማ ወሳኔ ላይ ይደረሳል ። ከሞት በኋላ የሚደረግ የጡረታ ውርስ ክፍፍልን ተከትሎ የሚነሳ ውዝግብ የተለመደም መሆኑን ወ/ሪት ግሬይ የሚናገሩ ሲሆን ፤ ብዙ ሰዎችም የተወሳሰበ የቤተሰብ ሁኔታ አላቸው ሲሉ ያስረዳሉ ።

“ ምናልባት ከአንድ በላይ ከሆነ ግንኙነት ልጆች ይኖራቸው ይሆናል ፤ህጋዊ የሆነ የትዳር አቻ ይኖራቸው ይሆናል ፤ ወይም ያለጋብቻ አብረዋቸው የሚኖሩ የኑሮ አጋርም እንዲሁ ፤ በቅርብ ካገቧቸ ሰው ታዳጊ ህጻናትን አፍርተውም ይሆናል ። ”

አብዛኛዎች የጡረታ ተቋማት ማስተላለፍ ወይም ማውረስ የሚፈልጉትን የገንዘብ መጠን በህግ ስምምነት እንዲያከፋፍሉ የሚፈቅድ አሰራር አላቸው ።

“ ይህ ህጋዊ ወረቀትም ከህልፈትዎ በኋላ የጡረታ ገንዘብዎን ማን መውሰድ እንዳለበት በግልጽ ያስቀምጥልዎታል ።”

" የጡረታ ገንዘብዎ እንዴት መከፋፈል እንዳለበት ጊዜ ወስደው ያስቡበት ፤ አስፈላጊ የሆኑ ህጋዊ ወረቀቶችን ቀድመው በማስገባት ሊነሱ የሚችሉ ውዝግቦችን ከወዲሁ ማስወገድ ይችላሉ ።”

Share